ከዚህ ተነሥተን ወደ ቤትኤል እንውጣ፤ በዚያም ከዚህ በፊት በተቸገርኩ ጊዜ ጸሎቴን ሰምቶ ለረዳኝና በሄድኩበት ስፍራ ሁሉ ከእኔ ላልተለየኝ አምላክ መሠዊያ እሠራለሁ።”
መዝሙር 66:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መከራ በደረሰብኝ ጊዜ “ለአንተ እሰጣለሁ” ያልኩትን ስእለት አቀርብልሃለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመከራ ጊዜ ከአፌ የወጣ፣ በከንፈሬም የተናገርሁት ስእለት ነው። |
ከዚህ ተነሥተን ወደ ቤትኤል እንውጣ፤ በዚያም ከዚህ በፊት በተቸገርኩ ጊዜ ጸሎቴን ሰምቶ ለረዳኝና በሄድኩበት ስፍራ ሁሉ ከእኔ ላልተለየኝ አምላክ መሠዊያ እሠራለሁ።”
ባልዋ ስለ ጉዳዩ ሰምቶ ስእለትዋን እንዳትፈጽም ቢከለክላት ግን የመፈጸም ግዴታ የለባትም፤ ስእለትዋን ለመፈጸም ያልቻለችው ባልዋ ስለ ከለከላት በመሆኑ እግዚአብሔር ይቅርታ ያደርግላታል።
አንድ ሰው ለእግዚአብሔር አንድ ነገር ለመስጠት ቢሳል ወይም ከአንድ ነገር ራሱን ለመከልከል በመሐላ ቃል ቢገባ፥ አደርጋለሁ ያለውን ሁሉ መፈጸም አለበት እንጂ የሰጠውን የተስፋ ቃል ማስቀረት አይገባውም።
ባልዋ ስለ ጉዳዩ ሰምቶ ከከለከላት ግን የመፈጸም ግዴታ የለባትም፤ ስእለትዋን ለመፈጸም ያልቻለችው ባልዋ ስለ ከለከላት በመሆኑ እግዚአብሔር ይቅርታ ያደርግላታል።
ሐናም እንዲህ ስትል ስእለት ተሳለች፦ “የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! እኔን አገልጋይህን ተመልከተኝ! መከራዬንም በማየት አስበኝ! አትርሳኝም! አንድ ወንድ ልጅ ብትሰጠኝ በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ለአንተ የተለየ እንዲሆን አደርገዋለሁ፤ ጠጒሩም ከቶ አይላጭም።”