Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 66:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 የሚቃጠል መሥዋዕት ይዤ ወደ ቤትህ እገባለሁ፤ ስእለቴንም አቀርብልሃለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 የሚቃጠል መሥዋዕት ይዤ ወደ መቅደስህ እገባለሁ፤ ስእለቴንም ለአንተ እፈጽማለሁ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13-14 ከሚቃጠል መሥዋዕት ጋር ወደ ቤትህ እገባለሁ፥ በመከራዬ ጊዜ በአፌ የተናገርሁትን በከንፈሮቼም ቃል የገባሁልህን ስእለቴን እፈጽማለሁ።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 66:13
19 Referencias Cruzadas  

እያመሰገናችሁ በመቅደሱ በሮች ግቡ፤ ምስጋናም በመስጠት ወደ አደባባዩ ሂዱ፤ አመስግኑት፤ ስሙንም አወድሱ።


አምላክ ሆይ! እኔ ራሴ ለአንተ የስእለት ግዴታ ገብቼአለሁ፤ ስእለቴን ከምስጋና መሥዋዕት ጋር አቀርባለሁ።


እንግዲህ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት የምስጋና መሥዋዕት ዘወትር ለእግዚአብሔር እናቅርብ፤ ይህም ስለ ስሙ በሚመሰክሩት ከንፈሮች የሚቀርብ የምስጋና መሥዋዕት ነው።


ስለዚህ እግዚአብሔር በሞኞች አይደሰትም፤ ለእግዚአብሔር አንድ ነገር ለመስጠት በተሳልክ ጊዜ ወዲያውኑ የተሳልከውን ለመፈጸም ዝግጁ ሁን፤


ወደ ውስጥ ገብቼ እግዚአብሔርን እንዳመሰግን የቤተ መቅደስን በሮች ከፈቱልኝ።


በሕዝብ ጉባኤ ፊት ተገኝቼ ለእግዚአብሔር የተሳልኩትን አቀርባለሁ።


እነሆ መልካም ዜናን የሚያበሥር፥ ሰላምንም የሚያውጅ መልእክተኛ በተራሮች ላይ እየመጣ ነው። የይሁዳ ሕዝብ ሆይ! ክፉዎች ጠላቶችህ ፈጽሞ ስለ ተደመሰሱ ከእንግዲህ ወዲህ አገርህን ከቶ አይወሩአትም! ስለዚህ ዓመት በዓሎችህን በደስታ አክብር! ስእለትህንም ለእግዚአብሔር ስጥ!


ደኅንነት ከእግዚአብሔር ነው፤ ስለዚህ ከምስጋና መዝሙር ጋር መሥዋዕትን ለአንተ አቀርባለሁ፤ የተሳልኩትንም እሰጣለሁ።”


እግዚአብሔር አምላክ ነው፤ ብርሃንን ሰጥቶናል፤ ለምለም የሆኑ ቅርንጫፎችን ይዘን በዓል ለማክበር ወደ መሠዊያው እንሂድ።


ስለ ሠራኸው መልካም ሥራ ብዙ ሕዝብ በተሰበሰበበት ስፍራ አመሰግንሃለሁ፤ በሚፈሩህ ሰዎች ፊት ሆኜ፥ የተሳልኩትን ስለት እፈጽማለሁ።


ይሁን እንጂ ለእግዚአብሔር ስእለት አለማድረግ ራሱ ኃጢአት አይደለም፤


ነገር ግን ለአምላክህ ለእግዚአብሔር በፍላጎትህ በተሳልከው መሠረት፥ አፍህ የተናገረውን በጥንቃቄ መፈጸም አለብህ።


“በአንድ ሰው የወይን ተክል መካከል በምታልፍበት ጊዜ ከፍሬው የምትፈልገውን ያኽል ብላ፤ ነገር ግን በማናቸውም ዕቃ ከፍሬው አትውሰድ።


ባያትም ጊዜ በሐዘን ልብሱን በመቅደድ “ወዮ ልጄ! ልቤን በሐዘን ሰበርሽው! ለታላቅ ጭንቀትም ዳረግሽኝ፤ ለእግዚአብሔር ቃል ገብቼአለሁና ስለቴን ልመልሰውም አልችልም፤” አለ።


ወደ እርሱም በምትጸልይበት ጊዜ የለመንከውን ሁሉ ስለሚፈጽምልህ፥ ስለትህን ትከፍላለህ።


አንተ ጸሎትን ሰሚ ስለ ሆንክ ሰዎች ሁሉ ወደ አንተ ይመጣሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios