በንጉሡ ዕድሜ ላይ ብዙ ዓመቶች ጨምርለት፤ ለብዙ ዘመንም እንዲኖር አድርገው!
የንጉሡን ዕድሜ አርዝምለት፤ ዘመኑንም እስከ ብዙ ትውልድ ጨምርለት፤
አቤቱ፥ አንተ ስእለቴን ሰምተሃልና፥ ስምህንም ለሚፈሩ ርስትን ሰጠሃቸው።
እርሱ አምላኬ መድኃኒቴም ነውና፤ እርሱ ረዳቴ ነውና፥ አልታወክም።
እግዚአብሔር ሆይ! ዕድል ፈንታዬና ጽዋዬ አንተ ነህ፤ ድርሻዬንም አስተማማኝ ታደርገዋለህ።
ለእኔ የተለኩልኝ የድንበር መስመሮች ያረፉት በሚያስደስቱ ቦታዎች ላይ ነው፤ በእርግጥ እኔ የሚያስደስት ርስት አለኝ።
ሕይወትን እንድትሰጠው ለመነህ፤ አንተም ረጅም ዕድሜና ዘለዓለማዊ የሆነ ሕይወትን ሰጠኸው።
የዘለዓለም በረከትን ሰጠኸው፤ አንተም ከእርሱ ጋር በመገኘትህ ደስ ታሰኘዋለህ፤
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ይሁን እንጂ በሕማም አደቀው ዘንድ የእኔ ፈቃድ ነበር፤ ሕይወቱን የበደል መሥዋዕት አድርጎ በሚያቀርብበት ጊዜ ዘመኑ ተራዝሞ ብዙ ትውልድ ያያል፤ በእርሱም አማካይነት የእኔ ፈቃድ ይፈጸማል።