መዝሙር 57:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነፍሴ ሆይ! ተነሺ፤ በገናዬና መሰንቆዬም ተነሡ! እኔም በማለዳ እነሣለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነፍሴ ሆይ፤ ንቂ! በገናና መሰንቆም ተነሡ! እኔም ማልጄ እነሣለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልቤ ጽኑ ነው፥ አቤቱ፥ ልቤ ጽኑ ነው፥ እቀኛለሁ፥ እዘምራለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደሚቀልጥ ሰም ያልቃሉ፤ እሳት ወደቀች፥ ፀሐይንም አላየኋትም። |
አሁን ግን በከበቡኝ ጠላቶቼ ላይ ራሴን ከፍ አደረግሁ፤ በደስታ “እልል” እያልኩ በመቅደሱ ውስጥ መሥዋዕት አቀርባለሁ፤ እየዘመርኩም እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ።
አምላክ ሆይ! ከዚያም በኋላ ለአንተ ለምታስደስተኝ ወደ መሠዊያህ ሄጄ እሰግድልሃለሁ፤ አንተ አምላኬ ነህ፤ በገናዬን እየደረደርኩ አመሰግንሃለሁ።
ጽዮን ሆይ! ተነሺ፤ ንቂ! ኀይልሽን እንደ ልብስ ልበሺ! ቅድስቲቱ ከተማ ኢየሩሳሌም ሆይ! የተዋበ ልብስሽን ልበሺ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ያልተገረዙና በሥርዓት ያልነጹ ሰዎች ወደ ቅጥርሽ ውስጥ አይገቡም።