አምላክ ሆይ! እኔ ራሴ ለአንተ የስእለት ግዴታ ገብቼአለሁ፤ ስእለቴን ከምስጋና መሥዋዕት ጋር አቀርባለሁ።
እግዚአብሔር ሆይ፤ የአንተ ስእለት አለብኝ፤ የማቀርብልህም የምስጋና መሥዋዕት ነው፤
በእግዚአብሔር ታመንሁ፥ አልፈራም፥ ሰው ምን ያደርገኛል?
እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ሆኖ ስለሚረዳኝ አልፈራም፤ ከቶ ሰው ምን ሊያደርገኝ ይችላል?
እውነተኛ ትእዛዞችህን ለመጠበቅ በመሐላ የገባሁትን ቃል አጸናለሁ።
እግዚአብሔር ሆይ! ልዕልናህ ከፍ ከፍ ይበል፤ ስለ ታላቁ ኀይልህም የምስጋና መዝሙር እናቀርባለን።
የምስጋና መሥዋዕት ለእግዚአብሔር አቅርብ፤ ስእለትህንም ለልዑል ስጥ።
መፈራት ለሚገባው ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ ተስላችሁ የተሳላችሁትን ስእለት ፈጽሙ፤ እናንተ በቅርብ ያላችሁ ሕዝቦች መባ አምጡለት።
በዚያን ዘመን እንዲህ ብለህ ትዘምራለህ፦ “ጌታ ሆይ! ቀድሞ ተቈጥተኸኝ ነበር፤ አሁን ግን ቊጣህን መልሰህ ስላጽናናኸኝ አመሰግንሃለሁ።
ሐናም እንዲህ ስትል ስእለት ተሳለች፦ “የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! እኔን አገልጋይህን ተመልከተኝ! መከራዬንም በማየት አስበኝ! አትርሳኝም! አንድ ወንድ ልጅ ብትሰጠኝ በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ለአንተ የተለየ እንዲሆን አደርገዋለሁ፤ ጠጒሩም ከቶ አይላጭም።”