እንደ ርግብ ክንፎች ቢኖሩኝ ዕረፍት ወደማገኝበት ስፍራ በርሬ መሄድን በወደድኩ ነበር።
እኔም እንዲህ አልሁ፤ “ምነው የርግብ ክንፍ በኖረኝ! በርሬ በሄድሁና ባረፍሁ ነበር፤
ፍርሃትና እንቅጥቅጥ መጡብኝ፥ መዘግነን ሸፈነኝ።
ይሸምቁብኛል፥ ይሸሸጉኝማል፥ እነርሱም ተረከዜን ይመለካከታሉ፥ ሁልጊዜም ነፍሴን ይሸምቁባታል።
እግዚአብሔር ከለላዬ ነው፤ እንዴት “እንደ ወፍ ወደ ተራራዎች ሽሽ” ትሉኛላችሁ።
ከፀሐይ መውጫ ባሻገር በርሬ ብሄድ፥ ወይም በፀሐይ መግቢያ በኩል ርቄ ብኖር፥
ራሴን ያዞረኛል፤ ከፍርሃት የተነሣም እንቀጠቀጣለሁ፤ ቀኑ ቶሎ እንዲመሽልኝ ተመኘሁ፤ ተስፋ ያደረግኹት ጭላንጭል አስደንጋጭ ሆነብኝ፦
ሴቲቱ በበረሓ ወደ ተዘጋጀላት ስፍራ በርራ እንድትሄድ የታላቅ ንስር ክንፎች የሚመስሉ ሁለት ክንፎች ተሰጡአት፤ እዚያም ከእባቡ ፊት ርቃ ሦስት ዓመት ተኩል በእንክብካቤ ተይዛ ትጠበቅ ነበር።