መዝሙር 55:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልቤ በውስጤ አስጨንቆኛል፤ የሞት ፍርሀትም ወደቀብኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልቤ በውስጤ ተጨነቀብኝ፤ የሞት ድንጋጤም በላዬ መጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከጠላት ድምፅ ከዓመፀኛም ግፍ የተነሣ፥ ዓመፃን በላዬ ጥለውብኛልና፥ በቁጣም ጠልተውኛልና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእግዚአብሔር ቃሉን አከብራለሁ፤ በእግዚአብሔር ታመንሁ፥ አልፈራም፤ ሰው ምን ያደርገኛል? |
ስድብ ልቤን ስለ ሰበረው ተስፋ ቈረጥኩ፤ የሚያስተዛዝነኝ ሰው ፈለግኹ፤ ነገር ግን ማንም አልነበረም፤ የሚያጽናናኝ ሰው ፈለግኹ፤ ነገር ግን ማንም አልተገኘም።
ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “እነሆ! ነፍሴ ተጨንቃለች፤ ምን ልበል? ‘አባት ሆይ! ከዚህች ሰዓት አድነኝ ልበልን?’ ይህን እንዳልል ግን እኔ የመጣሁት ለዚህች የመከራ ሰዓት ነው።
ኢየሱስ ሰው ሆኖ በዚህ ምድር በኖረበት ጊዜ ከሞት ሊያድነው ወደሚችል አምላክ በታላቅ ጩኸትና በብዙ እንባ ጸሎትንና ልመናን አቀረበ፤ በትሕትና ራሱን ታዛዥ በማድረጉ እግዚአብሔር ጸሎቱን ሰማው።