መዝሙር 5:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በአንተ ከለላ ሥር ያሉ ሁሉ ይደሰቱ፤ ለዘለዓለምም እልል ይበሉ የአንተን ስም የሚወዱትን ሁሉ በደስታም እንዲፈነድቁ ከልላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንተን መጠጊያ የሚያደርጉ ሁሉ ግን ደስ ይበላቸው፤ ዘላለም በደስታ ይዘምሩ፤ ስምህን የሚወድዱ በአንተ ደስ እንዲላቸው፣ ተከላካይ ሁንላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ ፍረድባቸው፥ በምክራቸውም ይውደቁ፥ ስለ ክፋታቸውም ብዛት አስወግዳቸው፥ እነርሱ ዐምፀውብሃልና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአንተ የሚታመኑት ሁሉ ግን ደስ ይላቸዋል፤ ለዘለዓለሙ ደስ ይላቸዋል፥ በእነርሱም ታድራለህ። ስምህንም የሚወድዱ ሁሉ በአንተ ይመካሉ። |
ድል ማድረጌ የሚያስደስታቸው ሁሉ ደስ ይበላቸው፤ “እግዚአብሔር ታላቅ ነው! ለአገልጋዩ ሁኔታዎች ሁሉ ሲሳኩለት እግዚአብሔር ደስ ይለዋል!” ይበሉ።
ጽዮን ሆይ! ደስ ይበልሽ! ኢየሩሳሌም ሆይ! በደስታ እልል በይ! እነሆ ንጉሥሽ ትሑት ሆኖ፥ በአህያይቱ ማለትም በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ፥ በድል አድራጊነት ወደ አንቺ ይመጣል።
ይሁን እንጂ መጽሐፍ፥ “የሰው ዐይን ያላየውን፥ የሰው ጆሮ ያልሰማውን፥ የሰው ልብ ያላሰበውን፥ እግዚአብሔር ለሚወዱት አዘጋጅቶአል” ይላል።
የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ስሙ፤ እግዚአብሔር በእምነት ሀብታሞች እንዲሆኑና እርሱን ለሚወዱት ተስፋ የሰጣቸውን መንግሥት እንዲወርሱ የዚህን ዓለም ድኾች አልመረጠምን?
ሰማይ ሆይ! በእርስዋ ደስ ይበልህ! እግዚአብሔር ስለ እናንተ በእርስዋ ላይ ስለ ፈረደባት እናንተ ቅዱሳንና ሐዋርያት ነቢያትም ደስ ይበላችሁ!
እግዚአብሔር ሆይ! ጠላቶችህን ሁሉ በዚህ ዐይነት አጥፋ፤ ወዳጆችህ ግን እንደ ንጋት ፀሐይ ይድመቁ። ከዚህ በኋላ በምድሪቱ ላይ አርባ ዓመት ሙሉ ሰላም ሆነ።