እዚያም ሳሉ በፍርሃት ተርበደበዱ፤ ምጥ እንደ ያዛትም ሴት ተጨነቁ።
ምጥ እንደ ያዛት ሴት፣ በዚያ ብርክ ያዛቸው።
እነርሱስ አይተው ተደነቁ፥ ደነገጡ፥ ሸሹም።
በኀይላቸው የሚታመኑ፥ በባለጠግነታቸውም ብዛት የሚኮሩ፤
ስለዚህም በዚያን ቀን ምሽት ሶርያውያን ድንኳኖቻቸውን፥ ፈረሶቻቸውንና አህዮቻቸውን በጠቅላላም ሰፈራቸውን ሁሉ እንዳለ ትተው ሕይወታቸውን ለማትረፍ ሸሽተው ሄደዋል።
በዚህም ምክንያት ሰውነቴ ታመመ፤ ምጥ እንደ ያዛት ሴትም አስጨነቀኝ፤ በምሰማው ነገር ታወክሁ፤ በማየውም ነገር ግራ ተጋባሁ።
ወዲያውኑ ፊቱ ገረጣ፤ ከድንጋጤውም ብዛት የተነሣ ጒልበቱ ተብረከረከ፤ የሰውነቱ መገጣጠሚያዎች ከዱት።
እስራኤል በሕይወት የመኖር ተስፋ አለው፤ ነገር ግን የሚወለድበት ጊዜ ሲቃረብ ከእናቱ ማሕፀን ለመውጣት እንደማይፈልግ ሕፃን ሞኝ ሆኖአል።