መዝሙር 46:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ከእርስዋ ጋር ስለ ሆነ ያቺ ከተማ አትናወጥም፤ ጠዋት በማለዳ እግዚአብሔር ይረዳታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር በመካከሏ ነው፤ አትናወጥም፤ አምላክ በማለዳ ይረዳታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የወንዝ ፈሳሾች የእግዚአብሔርን ከተማ ደስ ያሰኛሉ፥ ልዑል ማደሪያውን ቀደሰ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር በእልልታ፥ ጌታችንም በመለከት ድምፅ ዐረገ። |
የምተማመነው በአንተ ስለ ሆነ በየጠዋቱ ዘለዓለማዊ ፍቅርህን እንዳውቅ አድርገኝ፤ ሕይወቴን በዐደራ ለአንተ ስለ ሰጠሁ የምሄድበትን መንገድ አሳየኝ።
እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፥ ወደ ላይ ወደ መኖሪያህ በወጣህ ጊዜ ምርኮን ይዘህ ሄድክ፤ ከዐመፀኞች እንኳ ሳይቀር ከሰዎች ሁሉ ምርኮን ተቀበልክ።
ስለዚህ ሙሴ እጁን ወደ ባሕሩ ዘረጋ፤ ጎሕ ሲቀድ ውሃው ወደ ቀድሞ ቦታው ተመለሰ፤ ግብጻውያንም ከውሃው ሸሽተው ለመውጣት ሞከሩ፤ እግዚአብሔር ግን በባሕር ውስጥ ጣላቸው።
እርሱም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ! ይህ በእስራኤላውያን መካከል ለዘለዓለም በምኖርበት ዙፋኔና የእግሬ ማሳረፊያ ነው፤ እስራኤላውያንና ንጉሦቻቸው ከእንግዲህ ወዲህ ጣዖት በማምለክና በንጉሦቻቸው ሞት ጊዜ በሚያደርጉአቸው ድርጊቶች ስሜን አያሰድቡም።
ከእንግዲህ ወዲህ ግን ለጣዖቶች መስገዳቸውን ማቆምና የንጉሦቻቸውንም ሬሳ ከዚህ ማስወገድ አለባቸው፤ ይህን ቢያደርጉ እኔ በእነርሱ መካከል ለዘለዓለም እኖራለሁ።”
ከዚያም በኋላ ወደ ቤተ መቅደሱ መግቢያ መለሰኝ፤ እዚያም ከቤተ መቅደሱ መድረክ ሥር ውሃ ወደ ምሥራቅ ይፈስ ነበር፤ (ይህም የቤተ መቅደሱ በር ወደ ምሥራቅ ዞሮ ስለ ነበረ ነው) ውሃውም የሚፈሰው ከቤተ መቅደሱ በስተደቡብ በኩል ባለው መድረክ ሥር ከመሠዊያው በስተደቡብ ነበር።
እኔ በመካከላችሁ የምገኝ ቅዱሱ አምላክ ነኝ እንጂ ሰው አይደለሁም። ስለዚህ የቊጣዬን መቅሠፍት አላመጣም፤ ዳግመኛም እስራኤልን አላጠፋም፤ በቊጣዬም ወደ እናንተ አልመጣም።
ሕዝቤ ሆይ! እኔ በመካከላችሁ እንዳለሁ፥ አምላካችሁም እኔ ብቻ እንደ ሆንኩና ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ ታውቃላችሁ፤ ሕዝቤ ከእንግዲህ ወዲህ ኀፍረት አይደርስባቸውም።”
እግዚአብሔር በእናንተ ላይ ያስተላለፈውን የቅጣት ፍርድ አንሥቶላችኋል፤ ጠላቶቻችሁንም አስወግዶላችኋል፤ የእስራኤል ንጉሥ እግዚአብሔር በመካከላችሁ ነው፤ ከእንግዲህ ወዲህ ጥፋት ይደርስብናል ብላችሁ አትፈሩም።
እኔ እንድኖርባት ወደ ተቀደሰችው ከተማዬ ወደ ኢየሩሳሌም እመለሳለሁ፤ የታመነች ከተማ በመሆን ትታወቃለች፤ እኔ የሠራዊት አምላክ የምኖርበት ተራራ፥ የተቀደሰ ተራራ ተብሎ ይጠራል፤
ሰፈራችሁን በሕጉ መሠረት በንጽሕና ጠብቁ፤ እግዚአብሔር አምላካችሁ ሊጠብቃችሁና በጠላቶቻችሁም ላይ ድልን ሊያጐናጽፋችሁ በሰፈራችሁ ይገኛል፤ እግዚአብሔር ፊቱን ከእናንተ እንዲመልስ የሚያደርገውን አስነዋሪ ነገር ሁሉ አታድርጉ።
ለኤፌሶን ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦ “ይህ ሰባቱን ኮከቦች በቀኝ እጁ ከያዘውና በሰባቱ የወርቅ መቅረዞች መካከል ከሚመላለሰው የተነገረ ነው፤