መዝሙር 45:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፍላጻዎችህ የተሳሉ ናቸው፤ የጠላቶችህንም ልብ ይወጋሉ፤ መንግሥታትም ተሸንፈው በእግርህ ሥር ይወድቃሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሾሉ ፍላጻዎችህ በንጉሥ ጠላቶች ልብ ይሰካሉ፤ ሕዝቦችም ከእግርህ በታች ይወድቃሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ ቅንነትና ስለ የዋህነት ስለ ጽድቅም አቅና ተከናወን ንገሥም፥ ቀኝህም በክብር ይመራሃል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዳትታወክም እግዚአብሔር በመካከልዋ ነው፥ እግዚአብሔርም ፊት ለፊት ይረዳታል። |
እርሱ በሚነግሥበት ጊዜ የይሁዳ ሕዝብ ደኅንነት ያገኛል፤ የእስራኤልም ሕዝብ በሰላም ይኖራል፤ እርሱም ‘እግዚአብሔር ጽድቃችን’ ተብሎ ይጠራል።
ከግብጽ ያወጣቸው እግዚአብሔር ለእነርሱ እንደ ጐሽ ይዋጋላቸዋል፤ ጠላቶቻቸው የሆኑትን ሕዝቦች ይቦጫጭቅላቸዋል፤ አጥንቶቻቸውን ያደቃል፤ ቀስቶቻቸውንም ይሰባብራል።