እስራኤላውያንን ከሰጠኋቸው ምድር ተነቃቅለው እንዲባረሩ አደርጋለሁ፤ ስሜ እንዲጠራበት የቀደስኩትንም ይህን ቤተ መቅደስ እተወዋለሁ፤ በየአገሩ የሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ እስራኤልን መሳለቂያና መዘባበቻ ያደርጓታል።
መዝሙር 44:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ውርደቴ ዘወትር በፊቴ ነው፤ ፊቴንም ኀፍረት ሸፍኖታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ውርደቴ ቀኑን ሙሉ በፊቴ ነው፤ ፊቴም ዕፍረትን ተከናንቧል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአሕዛብ ዘንድ ምሳሌ፥ በሕዝብም ዘንድ መናቂያ አደረግኸን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በደስታና በሐሤት ይወስዱአቸዋል። ወደ ንጉሥ እልፍኝም ያስገቡአቸዋል። |
እስራኤላውያንን ከሰጠኋቸው ምድር ተነቃቅለው እንዲባረሩ አደርጋለሁ፤ ስሜ እንዲጠራበት የቀደስኩትንም ይህን ቤተ መቅደስ እተወዋለሁ፤ በየአገሩ የሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ እስራኤልን መሳለቂያና መዘባበቻ ያደርጓታል።
እግዚአብሔርም መልአክን ልኮ የአሦርን ወታደሮችና የጦር መኰንኖች እንዲገደሉ አደረገ፤ ስለዚህም የአሦር ንጉሠ ነገሥት ተዋርዶ ወደ አገሩ ተመለሰ፤ አንድ ቀን በአምላኩ መስገጃ ስፍራ በነበረበት ወቅት የገዛ ልጆቹ በሰይፍ ገደሉት።
“አምላኬ ሆይ፥ ኃጢአታችን ከራሳችን በላይ ስለ ሆነና በደላችንም ወደ ሰማይ ስለ ደረሰ ፊቴን ወደ አምላኬ ወደ አንተ ለማቅናት ዐፍራለሁ እፈራለሁም።
እኛና የቀድሞ አባቶቻችን በመደጋገም ኃጢአት በመሥራት እግዚአብሔር አምላካችንን አሳዝነናል፤ ትእዛዞቹንም አልፈጸምንም፤ ስለዚህ በዕፍረት ልንወድቅና ውርደትም እንደ ልብስ ሊሸፍነን ይገባል።”
‘ስለ ተሰደብን አፈርን፤ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ ወደ ተቀደሱ ስፍራዎች ባዕዳን ሰዎች ስለ ገቡ ተዋርደን አንገታችንን ደፋን።’ በሉ።
“ፍጹም ውብ ናት የሚሏት የዓለም መደሰቻ የነበረችው ከተማ ይህች ናትን?” እያሉ በመንገድ የሚያልፉ ሁሉ በኢየሩሳሌም ላይ እጃቸውን እያጨበጨቡ ራሳቸውን በመነቅነቅ አሽሟጠጡ።