45 ያለ ዕድሜው አስረጀኸው፤ በኀፍረትም ሸፈንከው።
45 የወጣትነት ዘመኑን አሳጠርኸው፤ ዕፍረትንም አከናነብኸው። ሴላ
45 በትረ መንግሥትን ሻርህ፥ ዙፋኑንም በምድር ላይ ጣልህ።
ከዚያን ጊዜም ጀምሮ ሰሜናዊው ክፍል እስራኤል በሚል ስም በዳዊት ሥርወ መንግሥት ላይ ዐመፀ።
እግዚአብሔር ገና ወጣት ሆኜ ሳለሁ ደካማ አደረገኝ፤ ሕይወቴንም አሳጠረ።
ጠላቶቼ ውርደትን እንደ ልብስ ይልበሱ፤ ኀፍረትንም እንደ መጐናጸፊያ ይደርቡ።
ውርደቴ ዘወትር በፊቴ ነው፤ ፊቴንም ኀፍረት ሸፍኖታል።
ተቃዋሚዎቼ ይፈሩ፤ ይጥፉም፤ ሊጐዱኝ የሚፈልጉ ይናቁ፤ ይዋረዱም።
ለጥቂት ጊዜ ቤተ መቅደስህ የቅዱስ ሕዝብህ ንብረት ነበር፤ አሁን ግን ጠላቶቻችን ረገጡት።
እግዚአብሔር በቊጣው ጽዮንን ምንኛ አዋረዳት! ወደ ሰማይ ከፍ ብላ የነበረችውን የእስራኤልን መመኪያ ወደ ምድር ጣላት፤ በቊጣው ቀን የእግሩ ማሳረፊያ መሆንዋን ሊያስታውስ አልፈቀደም።
ጠላቴም ይህን ሁሉ ያያል፤ “አምላክህ እግዚአብሔር የት አለ?” ይለኝ የነበረው ጠላቴ ኀፍረትን ይከናነባል፤ እኔ የጠላቴን ውድቀት አያለሁ፤ በመንገድ ዳር እንዳለ ጭቃ ሲረገጥም እመለከታለሁ።