በእኔ ላይ የሚመሰክሩ ሰዎች ዘወትር ታገኛለህ፤ በእኔ ላይ የምታሳየው ቊጣ እያደገ ይሄዳል፤ እኔን ለማጥቃት ዘወትር አዳዲስ ዕቅዶችን እንደ ሠራዊት ታሰልፍብኛለህ።
መዝሙር 42:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በፏፏቴህ ድምፅ ጥልቁ ጥልቁን ይጠራል፤ ማዕበልህና ሞገድህ በእኔ ላይ አለፈ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በፏፏቴህ ማስገምገም፣ አንዱ ጥልቅ ሌላውን ጥልቅ ይጣራል፤ ማዕበልህና ሞገድህ ሁሉ፣ ሙሉ በሙሉ አጥለቀለቀኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አምላኬ ሆይ፥ ነፍሴ በእኔ ውስጥ ታወከች፥ ስለዚህ በዮርዳኖስ ምድር በአርሞንኤምም በታናሹ ተራራ አስታውስሃለሁ። |
በእኔ ላይ የሚመሰክሩ ሰዎች ዘወትር ታገኛለህ፤ በእኔ ላይ የምታሳየው ቊጣ እያደገ ይሄዳል፤ እኔን ለማጥቃት ዘወትር አዳዲስ ዕቅዶችን እንደ ሠራዊት ታሰልፍብኛለህ።
መቅሠፍት በመቅሠፍት ላይ ይደራረባል፤ አገሪቱ በሙሉ ፈራርሳ ጠፍ ሆናለች፤ ድንኳኖቻችን በድንገት ወደሙ፤ መጋረጃዎቻቸውም በቅጽበት ተቀደዱ።
አንዱ መቅሠፍት ሌላውን ያስከትላል፤ አንዱ ወሬም ሌላውን ወሬ ተከታትሎ ይመጣል፤ ነቢያት ያዩትን ራእይ እንዲነግሩአችሁ ትለምኑአቸዋላችሁ፤ ካህናት ሕዝቡን የሚያስተምሩት ሕግ፥ ሽማግሌዎችም ለሕዝቡ የሚሰጡት ምክር ጠፋባቸው።