መዝሙር 41:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ይጠብቃቸዋል፤ በሕይወትም ያኖራቸዋል፤ በምድር ላይ ይባርካቸዋል፤ ለጠላቶቻቸውም አሳልፎ አይሰጣቸውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ይጠብቀዋል፤ በሕይወትም ያኖረዋል፤ በምድርም ላይ ይባርከዋል፤ ለጠላቶቹም ምኞት አሳልፎ አይሰጠውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለችግረኛና ለምስኪን የሚያስብ ምስጉን ነው፥ ጌታ በክፉ ቀን ያድነዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነፍሴ ወደ ሕያው አምላኬ ተጠማች፤ መቼ እደርሳለሁ? የአምላኬንስ ፊት መቼ አያለሁ? |
በከተሞቻችሁ የሚኖሩ ከእናንተ ጋር የተካፈሉት ርስት የሌላቸው ሌዋውያን፥ የውጪ አገር ስደተኞች፥ እናትና አባት የሌላቸው የሙት ልጆችና ባሎቻቸው የሞቱባቸው መጥተው ይብሉ፤ ይህን ሁሉ ብታደርጉ አምላካችሁ እግዚአብሔር በምትሠሩት ነገር ሁሉ ይባርካችኋል።
በሰውነት ማጠንከሪያ ትምህርት ራስን ማለማመድ ጥቅሙ ጥቂት ነው፤ እግዚአብሔርን ማምለክ ማለማመድ ግን ለአሁንና ለሚመጣው ሕይወት ተስፋ ስላለው ለሁሉ ነገር ይጠቅማል።
ዐማትዋ “ዛሬ ከየት ቃረምሽ? ወደየትስ ሠራሽ? ይህን መልካም አቀባበል ያደረገልሽን ሰው እግዚአብሔር ይባርከው!” አለቻት። ሩትም “እኔ ስቃርም የዋልኩበት እርሻ ባለቤት ቦዔዝ የሚባል ሰው ነው” ብላ ለናዖሚ ነገረቻት።