እኔን ድል በማድረጋቸው እንደ ተደሰቱ አይቀሩም፤ አንተም በእኔ ደስ እንደ ተሰኘህ ዐውቃለሁ።
ጠላቴ በላዬ ድል አላገኘምና፣ እንደ ወደድኸኝ በዚህ ዐወቅሁ።
አንተ ግን አቤቱ፥ ማረኝ፥ እመልስላቸውም ዘንድ አቁመኝ።
ነፍሴ ሆይ፥ ለምን ታዝኛለሽ? ለምንስ ታውኪኛለሽ? የፊቴን መድኀኒት አምላኬን አመሰግነው ዘንድ በእግዚአብሔር ታመኚ።
ጠላቶቻችን እንዲደመስሱን ያላደረገ እግዚአብሔር ይመስገን።
ጠላቶቼ “አሸነፍነው” ብለው እንዲመኩ፥ በእኔም መውደቅ ደስ እንዲላቸው አታድርግ።
እርሱን ደስ የሚያሰኙት በአክብሮት የሚፈሩትና በዘለዓለማዊ ፍቅሩ የሚታመኑ ሰዎች ናቸው።
አምላኬ ሆይ! በአንተ እታመናለሁ፤ ጠላቶቼ ድል እንዲቀዳጁ አድርገህ አታሳፍረኝ።
ለጠላቶች አሳልፈህ አልሰጠኸኝም፤ ነገር ግን ሰፊ መንገድ ከፈትክልኝ።
“ይኸዋ የልባችን ምኞት ደረሰ!” ብለው እንዲያስቡና ወይም “እኛ አሸነፍነው!” እንዲሉ አታድርግ።
እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ስለ ረዳኸኝና ስላጽናናኸኝ፥ ጠላቶቼ አይተው ያፍሩ ዘንድ፥ ለእኔ ሞገስን የመስጠት ምልክትህን አሳየኝ።
ለእግዚአብሔር ዘምሩ! ጌታን አመስግኑ! እርሱ ችግረኞችን ከክፉ ሰዎች ኀይል ይታደጋል።
ኀይሎችንና ባለሥልጣኖችን በመስቀሉ ድል ነሥቶ ትጥቃቸውን ካስፈታ በኋላ ምርኮኞች ሆነው በይፋ እንዲታዩ አደረጋቸው።