La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መዝሙር 38:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከቊጣህ የተነሣ ሥጋዬ ደኅንነት የለውም። በኃጢአቴም ምክንያት መላ ሰውነቴ ጤንነት የለውም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከቍጣህ የተነሣ ሰውነቴ ጤና አጥቷል፤ ከኀጢአቴም የተነሣ ዐጥንቶቼ ሰላም የላቸውም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ፍላጾችህ ወግተውኛልና፥ እጅህንም በላዬ ላይ አክብደህብኛልና።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ልቤም በው​ስጤ ሞቀ​ብኝ፤ ከመ​ና​ገ​ሬም የተ​ነሣ እሳት ነደደ፥ በአ​ን​ደ​በ​ቴም ተና​ገ​ርሁ፦

Ver Capítulo



መዝሙር 38:3
13 Referencias Cruzadas  

ዕጣን ለማጠን ዝግጁ ሆኖ ጥናውን በእጁ እንደ ያዘ በቤተ መቅደሱ ውስጥ በዕጣን መሠዊያው አጠገብ ቆሞ የነበረው ዖዝያም በካህናቱ ላይ እጅግ ተቈጣ፤ ወዲያውኑ በግንባሩ ላይ የቆዳ በሽታ ታየ።


ሁሉን የሚችል አምላክ በፍላጻዎቹ ወግቶኛል፤ መርዛቸውም በሰውነቴ ተሠራጭቶአል፤ የሚያስደነግጥ የእግዚአብሔር መቅሠፍት ዙሪያዬን ከቦኛል።


የሕይወት ዘመኔ እንደ ጢስ እየበነነ በማለቅ ላይ ነው፤ ሰውነቴም እንደ እሳት እየነደደ ነው።


ድምፄን ከፍ አድርጌ በመቃተቴ ከቈዳና ከአጥንት በቀር ሰውነት የለኝም።


ቀንና ሌሊት በብርቱ ቀጣኸኝ፤ ርጥበት ያለው ነገር በበጋ ሙቀት እንደሚደርቅ ጒልበቴ በፍጹም አለቀ።


የሰበርካቸውን አጥንቶቼን አድሰህ የደስታንና የሐሤትን ድምፅ አሰማኝ፤


እግዚአብሔር ሆይ! ደካማ ስለ ሆንኩ ምሕረት አድርግልኝ፤ ጌታ ሆይ! ደካማ ሰውነቴ እየተሠቃየ ስለ ሆነ፥ እባክህ ፈውሰኝ።