ፋታ ከማይሰጠው ሕመሜ የተነሣ ተዝለፍልፌ ልወድቅ ተቃርቤአለሁ።
ልወድቅ ተቃርቤአለሁ፤ ከሥቃዬም ከቶ አልተላቀቅሁም።
ጠላቶቼ በእኔ ላይ ደስ እንዳይላቸው ብያለሁና፥ እግሮቼም ቢሰናከሉ ራሳቸውን በእኔ ላይ ከፍ ከፍ ያደርጋሉ።
እኔ በማያቋርጥ ፍቅርህ እተማመናለሁ፤ በማዳንህ እደሰታለሁ።
በተደናቀፍኩ ጊዜ ደስ ብሎአቸው ተሰባሰቡ፤ የማላውቃቸው ጋጠወጦች መጥተው ያለማቋረጥ አላገጡብኝ።
ያለ ምክንያት የሚጠሉኝ ጠላቶቼ በእኔ ምክንያት እንዲደሰቱ አታድርግ፤ በኋላዬ ሆነው እንዲጠቃቀሱብኝም አታድርግ።
ጐበጥኩ፤ እጅግም እያጐነበስኩ ሄድኩ፤ ቀኑን ሙሉ በትካዜ አሳለፍኩ።
ከሐዘኔ ብዛት የተነሣ ደክሜአለሁ፤ ከለቅሶዬ ብዛት የተነሣ በየሌሊቱ አልጋዬ በእንባ ይረጥባል፤ ትራሴም ይርሳል።