መዝሙር 37:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ክፉዎች ሰዎች የሚጠፉበት ቀን እንደ ተቃረበ ስለሚያውቅ እግዚአብሔር በእነርሱ ይስቃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ግን ይሥቅባቸዋል፣ ቀናቸው እንደ ደረሰ ያውቃልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ግን ይሥቅበታል፥ ቀኑ እንደሚደርስ አይቶአልና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ ግን እንደማይሰማ ደንቆሮ፥ አፉንም እንደማይከፍት ዲዳ ሆንሁ። |
ወታደሮቻቸውን፥ ወደ ማረጃ ቦታ ወርደው እንደሚታረዱ የዕርድ ኰርማዎች ወስዳችሁ ግደሉ፤ የሚቀጡበት ጊዜ ስለ ደረሰ ለባቢሎን ሕዝብ ወዮላቸው!
የምታዩት ራእይ ሐሰት ነው፤ የምትናገሩትም የትንቢት ቃል ውሸት ነው፤ እናንተ ክፋትና ርኲሰት የሞላችሁ ናችሁ፤ ለመጨረሻ ጊዜ ቅጣት የምትቀበሉበት ቀን ቀርቦአል፤ በአንገታችሁ ላይ ሰይፍ ተቃጥቶአል።
በሕያው እግዚአብሔር ስም እምልልሃለሁ፤ እግዚአብሔር ራሱ ሳኦልን ይገድለዋል፤ የሚሞትበት ጊዜ ደርሶ፥ አለበለዚያም በጦርነት መሞቱ አይቀርም፤