መዝሙር 36:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በቤትህ የተትረፈረፈውን ምግብ ይጋበዛሉ፤ አስደሳች ከሆነ ወንዝህም ታጠጣቸዋለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከቤትህ ሲሳይ ይመገባሉ፤ ከበረከትህም ወንዝ ይጠጣሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ ጽኑ ፍቅርህን እንዴት አበዛህ! የሰው ልጆች በክንፎችህ ጥላ ይታመናሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መዓትን ተዋት፤ ቍጣንም ጣላት፥ እንዳትበድልም አትቅና። |
አንተ የመረጥካቸውና በተቀደሰ አደባባይህ እንዲኖሩ ወደ ራስህ ያቀረብካቸው፥ ደስ ይበላቸው፤ እኛም ከቤትህ በሚገኘው መልካም ነገርና ከመቅደስህ በሚገኘው በረከት እንረካለን።
እኅቴ ሙሽራዬ ሆይ! እነሆ ወደ አትክልት ቦታዬ ገባሁ፤ ከርቤዬንና የሽቶ አበባዎቼን ለቀምኩ፤ የማር ሰፈፌን ከወለላው ጋር ተመገብኩ፤ የወይን ጠጄንና ወተቴንም ጠጣሁ። ወዳጆቼ ሆይ! በፍቅር እስክትረኩ ድረስ ብሉ፥ ጠጡ።
የሠራዊት አምላክ በዚህች በጽዮን ተራራ ለዓለም ሕዝቦች ሁሉ ታላቅ ግብዣ ያዘጋጃል፤ በግብዣውም ላይ ምርጥ የወይን ጠጅና፥ የተሟላ ምግብ ይዘጋጃል።
ለተመረጡት ሕዝቤ ውሃን ለመስጠት ወንዞች በበረሓ ጅረቶች በምድረ በዳ እንዲፈስሱ ባደረግሁ ጊዜ የምድር አራዊት እንኳ ሳይቀሩ ያከብሩኛል፤ ቀበሮዎችና ሰጎኖችም ያመሰግኑኛል።
እግዚአብሔር በምድረ በዳ በመራቸው ጊዜ ውሃ አልጠማቸውም፤ ይልቁንስ ውሃ ከአለት እንዲፈልቅላቸው አደረገ። አለቱን ከፍሎ ውሃ አጐረፈላቸው።
እኔ ሁልጊዜ እመራችኋለሁ፤ በድርቅም ቦታ ፍላጎታችሁን አረካለሁ፤ አጥንታችሁንም አጠነክራለሁ፤ ውሃ እንደሚጠጣ የአትክልት ቦታና ደርቆ እንደማያውቅ ምንጭ ትሆናላችሁ።