መዝሙር 35:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ይኸዋ! ይኸዋ! እኛ ራሳችን የሠራኸውን አየን!” እያሉ በመጮኽ ያሳጡኛል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አፋቸውን አስፍተው ከፈቱብኝ፤ “ዕሠይ! ዕሠይ! በዐይናችን አየነው” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አፋቸውንም በእኔ ላይ አላቀቁ፥ እሰይ እሰይ፥ ዓይናችን አየው ይላሉ። |
እርሱ ከምሥራቅ ሶርያውያንን፥ ከምዕራብ ፍልስጥኤማውያንን ልኮ እስራኤልን እንዲወሩ አደረገ፤ ይህም ሁሉ ሆኖ ቊጣው አልበረደም፤ ስለዚህ እጁ እነርሱን ለመቅጣት እንደ ተቃጣ ነው።
ጠላቶቻችሁ ሁሉ በእናንተ ላይ አፋቸውን ይከፍታሉ፤ ያሽሟጥጣሉ ጥርሳቸውን ያፋጫሉ፤ እንዲህ ሲሉም ይጮኻሉ፦ “ደመሰስናቸው! እሰይ ይህ የምንመኘው ቀን ነበር! በመጨረሻም አየነው።”
ለአሞናውያን፥ ጌታ እግዚአብሔር የሚለውን ስሙ በላቸው፦ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ቤተ መቅደሴ እንዲረክስ በተደረገ ጊዜ፥ የእስራኤል ምድር ባድማ በሆነ ጊዜ፥ የይሁዳ ሕዝብ ተማርኮ በተወሰደ ጊዜ እሰይ ብላችኋል።