La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መዝሙር 35:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ያለ ምክንያት የሚጠሉኝ ጠላቶቼ በእኔ ምክንያት እንዲደሰቱ አታድርግ፤ በኋላዬ ሆነው እንዲጠቃቀሱብኝም አታድርግ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከምድር ተነሥተው ጠላቶቼ የሆኑት፣ በላዬ ደስ አይበላቸው፤ እንዲያው የሚጠሉኝ፣ በዐይናቸው አይጣቀሱብኝ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከሐዲ ጠላቶቼ በእኔ ደስ አይበላቸው፥ በከንቱ የሚጣሉኝም በዓይናቸው አይጠቃቀሱብኝ።

Ver Capítulo



መዝሙር 35:19
19 Referencias Cruzadas  

ልብህ ለምን ወደ ሌላ ይወስድሃል? ስለምንስ በቊጣ ዐይኖችህን ታፈጣለህ?


በጥላቻ ዙሪያዬን ከበቡኝ፤ ያለ ምክንያትም አደጋ ጣሉብኝ


ባለሥልጣኖች ያለ ምክንያት ያሳድዱኛል፤ እኔ ግን ቃልህን በፍርሃት አከብራለሁ።


ጠላቶቼ “አሸነፍነው” ብለው እንዲመኩ፥ በእኔም መውደቅ ደስ እንዲላቸው አታድርግ።


አምላኬ ሆይ! በአንተ እታመናለሁ፤ ጠላቶቼ ድል እንዲቀዳጁ አድርገህ አታሳፍረኝ።


በተደናቀፍኩ ጊዜ ደስ ብሎአቸው ተሰባሰቡ፤ የማላውቃቸው ጋጠወጦች መጥተው ያለማቋረጥ አላገጡብኝ።


“ጠላቶቼ እኔን በንቀት ዐይን እንዲመለከቱኝ ወይም እግሬን ሲያዳልጠው ራሳቸውን ከፍ እንዲያደርጉ አታድርግ!” ብዬ እለምናለሁ።


ፋታ ከማይሰጠው ሕመሜ የተነሣ ተዝለፍልፌ ልወድቅ ተቃርቤአለሁ።


ያለ ምክንያት ጠላት የሆኑብኝ ኀያላን ናቸው፤ በስሕተትም የሚጠሉኝ ብዙዎች ናቸው።


እኔ ደግ ሥራ በመሥራቴ በመልካም ፈንታ ክፉ የሚመልሱልኝ፤ በእኔ ላይ በጠላትነት ተነሥተዋል።


ያለ ምክንያት የሚጠሉኝ ከራሴ ጠጒር ይልቅ በዝተዋል፤ ብዙዎች ጠላቶቼ ሊያጠፉኝ ይፈልጋሉ ያልሰረቅኹትን ነገር መመለስ አለብኝን?


አምላክ ሆይ! ሞኝነቴን አንተ ታውቃለህ፤ ኃጢአቴ ከአንተ የተሰወረ አይደለም።


በሰው ላይ መጠቃቀስ ችግርን ያመጣል፤ በግልጥ የሚነቅፍ ግን ሰላም እንዲገኝ ያደርጋል።


እርሱም፥ ለማታለል በዐይኑ ይጠቅሳል፤ በእግሩ ያመለክታል፤ በእጁ ይጠቊማል።


“ያለ ምክንያት የሚጠሉኝ ጠላቶቼ እንደ ወፍ አጠመዱኝ።


ይህም የሆነው፥ ‘ያለ ምክንያት ጠሉኝ’ ተብሎ በሕጋቸው የተጻፈው ቃል እንዲፈጸም ነው።