Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መዝሙር 35:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ከሐዲ ጠላቶቼ በእኔ ደስ አይበላቸው፥ በከንቱ የሚጣሉኝም በዓይናቸው አይጠቃቀሱብኝ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ከምድር ተነሥተው ጠላቶቼ የሆኑት፣ በላዬ ደስ አይበላቸው፤ እንዲያው የሚጠሉኝ፣ በዐይናቸው አይጣቀሱብኝ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ያለ ምክንያት የሚጠሉኝ ጠላቶቼ በእኔ ምክንያት እንዲደሰቱ አታድርግ፤ በኋላዬ ሆነው እንዲጠቃቀሱብኝም አታድርግ።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 35:19
19 Referencias Cruzadas  

ልብህስ ለምን ወደ ሌላ ይወስድሃል? ዐይኖችህስ ለምን ይገላምጣሉ?


በጥላቻ ቃል ከበቡኝ፥ በከንቱም አጠቁኝ።


ገዢዎች በከንቱ አሳደዱኝ፥ ከቃልህ የተነሣ ግን ልቤ ደነገጠብኝ።


አቤቱ አምላኬ፥ እየኝ ስማኝም፥ ለሞትም እንዳልተኛ ዐይኖቼን አብራ


አምላኬ፥ በአንተ ታመንሁ፥ አልፈር፥ ጠላቶቼ በእኔ አይሣቁብኝ።


በእኔ ላይ ተሰበሰቡ ደስም አላቸው፥ ግፈኞች በእኔ ላይ ተሰበሰቡ እኔም አላወቅሁም፥ መቦጫጨቃቸውን አላቆሙም።


አቤቱ፥ በአንተ ታምኛለሁና፥ አቤቱ አምላኬ፥ አንተ ትሰማኛለህ።


ጠላቶቼ በእኔ ላይ ደስ እንዳይላቸው ብያለሁና፥ እግሮቼም ቢሰናከሉ ራሳቸውን በእኔ ላይ ከፍ ከፍ ያደርጋሉ።


በደሌን እናገራለሁና፥ ስለ ኃጢአቴም እተክዛለሁ።


ጠላቶቼ ሕያዋን ናቸው ይበረቱብኝማል፥ በጠማማነትም የሚጠሉኝ በዙ።


በጩኸት ደከምሁ ጉሮሮዬም ሰለለ፥ አምላኬን ስጠብቅ ዐይኖቼ ፈዘዙ።


በከንቱ የሚጠሉኝ ከራሴ ጠጉር በዙ፥ በዓመፅ ያሚያሳድዱኝ ጠላቶቼ በረቱ፥ በዚያን ጊዜ ያልቀማሁትን መለስሁ።


በዓይኑ የሚጠቅስ መከራን ያመጣል፥ ደፍሮ የሚገሥጽ ግን ሰላምን ያደርጋል።


በዓይኑ ይጠቅሳል፥ በእግሩ ይናገራል፥ በጣቱ ያስተምራል፥


ጻዴ። በከንቱ ነገር ጠላቶች የሆኑኝ እንደ ወፍ ማደንን አደኑኝ።


ነገር ግን በሕጋቸው ‘በከንቱ ጠሉኝ’ ተብሎ የተጻፈው ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos