በምድርም የምትኖሩ ሁሉ እግዚአብሔርን ፍሩ፤ የዓለም ሕዝቦች ሁሉ እግዚአብሔርን አክብሩ።
ምድር ሁሉ እግዚአብሔርን ትፍራው፤ በዓለም የሚኖር ሕዝብ ሁሉ በፊቱ ይንቀጥቀጥ።
ምድር ሁሉ ጌታን ትፍራው፥ በዓለም የሚኖሩ ሁሉ ይደንግጡ።
እግዚአብሔር ቸር እንደ ሆነ ቅመሱ፥ ዕወቁም፤ በእርሱ የሚታመን ሰው ብፁዕ ነው።
በሐሳባቸው ጠቢባን ነን የሚሉትን ስለሚንቃቸው ሰዎች ሁሉ ይፈሩታል።”
እስከ ምድር ዳርቻ ያሉ ሰዎች ሁሉ አስታውሰው ወደ እግዚአብሔር ይመለሳሉ፤ በዓለም የሚገኙት ሕዝቦች ሁሉ በፊቱ ይሰግዳሉ።
እግዚአብሔር ስለሚባርከንም በምድር ዳርቻ ያሉ ሁሉ ይፈሩታል።
እግዚአብሔር ሆይ አንተ ግን በሁሉ ዘንድ የተፈራህ ነህ፤ አንተ ስትቈጣ በፊትህ የሚቆም አንድ እንኳ አይኖርም፤
አምላካችን እንደሚያቃጥል እሳት ነው።
ጌታ ሆይ! አንተን የማይፈራና ስምህንም የማያከብር ማን ነው? አንተ ብቻ ቅዱስ ነህ፤ የእውነት ፍርድህ ስለ ተገለጠ፥ ሕዝቦች ሁሉ መጥተው በፊትህ ይሰግዳሉ።”