መዝሙር 33:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባሕርን ሁሉ በአንድ ቦታ ሰበሰበ፤ ጥልቅ ለሆኑት ውቅያኖሶችም መከማቻ ስፍራ አዘጋጀላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የባሕርን ውሃ በአንድ ዕቃ ይሰበስባል፤ ቀላዩንም በአንድ ስፍራ ያከማቻል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የባሕርን ውኃ በኰዳ የሚሰበስበው፥ ቀላዮችንም በመዝገቦች የሚያኖራቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፥ ያድናቸውማል። |
እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ታዲያ ስለምን አታከብሩኝም? በፊቴስ ለምን አትንቀጠቀጡም፤ አሸዋን ውሃ አልፎት እንዳይሄድ ለዘለዓለሙ የባሕር ወሰን ያደረግኹት እኔ ነኝ፤ ባሕር የቱንም ያኽል ቢናወጥ፥ ማዕበል፥ ሞገዱም ቢያስገመግም፥ ወሰን የሆነውን የአሸዋ ግድብ አልፎ መሄድ አይችልም።
የምድርን ሁሉ ጌታ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት የተሸከሙ ካህናት እግሮች ውሃውን በሚነኩበት ጊዜ የዮርዳኖስ ወንዝ ውሃ መውረዱን ያቆማል፤ ከላይ እየጐረፈ የሚመጣውም ውሃ በአንድ ቦታ ተሰብስቦ ይቈለላል።”
ውሃው መውረዱን አቆመ፤ በጻርታን አጠገብ አዳም ተብላ እስከምትጠራው ከተማ ድረስ ተከመረ፤ ወደ ሙት ባሕር ይፈስ የነበረውም ጐርፍ በፍጹም ተቋረጠ፤ ስለዚህም ሕዝቡ ወደ ማዶ ወደ ኢያሪኮ ተሻገሩ።