መዝሙር 30:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ የሚቈጣው ለጥቂት ጊዜ ነው፤ ቸርነቱ ግን ለዘለዓለም ነው፤ ሌሊት ሲለቀስ ዐድሮ በማለዳ ደስታ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቍጣው ለዐጭር ጊዜ ነው፤ ቸርነቱ ግን እስከ ዕድሜ ልክ ነውና፤ ሌሊቱን በልቅሶ ቢታደርም፣ በማለዳ ደስታ ይመጣል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቅዱሳን ሆይ፥ ለጌታ ዘምሩ፥ ለቅድስናውም መታሰቢያ አመስግኑ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእጅህ ነፍሴን አደራ እሰጣለሁ፤ የጽድቅ አምላክ እግዚአብሔር፥ ተቤዠኝ። |
የምተማመነው በአንተ ስለ ሆነ በየጠዋቱ ዘለዓለማዊ ፍቅርህን እንዳውቅ አድርገኝ፤ ሕይወቴን በዐደራ ለአንተ ስለ ሰጠሁ የምሄድበትን መንገድ አሳየኝ።
እግዚአብሔርም እንደገና ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ለእስራኤል ሕዝብ እንዲህ በላቸው፦ የአባቶቻችሁ የአብርሃም፥ የይስሐቅ፥ የያዕቆብ አምላክ እግዚአብሔር ወደ እናንተ ልኮኛል፤ ይህ የዘለዓለም ስሜ ነው፤ በዚህም ስም ከትውልድ እስከ ትውልድ እታወቃለሁ።
ኑ፤ እግዚአብሔርን እንወቅ፤ ሳናወላውልም እንከተለው፤ እርሱም እንደ ንጋት ብርሃንና ምድርን እንደሚያረካ የበልግ ዝናም በእርግጥ ወደ እኛ ይመጣል።”
መንፈስ ቅዱስና ሙሽራይቱ “ና!” ይላሉ፤ የሚሰማም “ና!” ይበል፤ የተጠማም ይምጣ፤ የፈለገም የሕይወትን ውሃ ያለ ምንም ዋጋ በነጻ ይጠጣ።