በማለዳ እየተነሡና በምሽትም እየዘገዩ ለኑሮ መድከም ከንቱ ነው፤ እግዚአብሔር ለሚወዳቸው ሰዎች ገና ተኝተው ሳሉ የሚያስፈልጋቸውን ነገር ያዘጋጅላቸዋል።
መዝሙር 3:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ ተኛሁ፥ አንቀላፋሁም፤ እግዚአብሔር ሌሊቱን ሙሉ ስለ ጠበቀኝ ከእንቅልፌ ተነሣሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እተኛለሁ፤ አንቀላፋለሁ፤ እግዚአብሔር ደግፎ ይዞኛልና እነቃለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሙሉ ድምጽ ወደ ጌታ እጮሃለሁ፥ ከተቀደሰ ተራራውም ይሰማኛል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ ተኛሁ፤ አንቀላፋሁም፤ እግዚአብሔርም አንሥቶኛልና ተነሣሁ። |
በማለዳ እየተነሡና በምሽትም እየዘገዩ ለኑሮ መድከም ከንቱ ነው፤ እግዚአብሔር ለሚወዳቸው ሰዎች ገና ተኝተው ሳሉ የሚያስፈልጋቸውን ነገር ያዘጋጅላቸዋል።
“በምድራችሁ ሰላምን እሰጣችኋለሁ፤ ማንንም ሳትፈሩ ያለ ስጋት ትተኛላችሁ፤ አደገኞች የሆኑ አራዊትን ከምድራችሁ አስወግዳለሁ፤ ከእንግዲህም ወዲህ ጦርነት በዚያ አይኖርም።
ሄሮድስ በማግስቱ ጴጥሮስን ለሕዝቡ ሊያቀርበው አስቦ ነበር፤ ጴጥሮስም በዚያች ሌሊት በሁለት ሰንሰለት ታስሮ በሁለት ወታደሮች መካከል ተኝቶ ነበር፤ ሌሎች ወታደሮችም የወህኒ ቤቱን በር ይጠብቁ ነበር።