የሊባኖስን ተራራዎች እንደ እንቦሳ እንዲፈነጩ ያደርጋቸዋል፤ የስርዮንንም ተራራ እንደ ጐሽ ጥጃ እንዲዘል ያደርገዋል።
ሊባኖስን እንደ ጥጃ፣ ሢርዮንንም እንደ አውራሪስ ግልገል ያዘልላል።
እንደ ጥጃ ሊባኖስን፥ እንደ ጎሽ ጥጃ ስርዮንን ያዘልላቸዋል።
እኔም በደስታዬ፥ “ለዘለዓለም አልታወክም” አልሁ።
አንተ እንደ ጐሽ ቀንድ ከፍ አደረግኸኝ፤ በትኲስ ዘይትም ቀባኸኝ።
ከግብጽ ምድር ያወጣቸው እግዚአብሔር እርሱ ለእነርሱ እንደ ጎሽ ቀንድ ይዋጋላቸዋል፤
የሔርሞንን ተራራ ሲዶናውያን ሢርዮን ብለው ሲጠሩት፥ አሞራውያን ‘ሠኒር’ ብለው ሰይመውታል።
ከዚህ በኋላ ታላቅ ነጭ ዙፋንና በዙፋኑም ላይ የተቀመጠውን አየሁ፤ ምድርና ሰማይ ከፊቱ ሸሹ፤ ስፍራም አልተገኘላቸውም፤