ምንም እንኳ እኔ እግዚአብሔር መርጦ የሾመኝ ንጉሥ ብሆን ዛሬ ደካማነት ተሰምቶኛል፤ እነዚህ የጸሩያ ልጆች በእኔ ላይ እጅግ የበረቱ ዐመፀኞች ሆነውብኛል፤ እነዚህን ነፍሰ ገዳዮች እግዚአብሔር ራሱ የሚገባቸውን ቅጣት ይስጣቸው!”
መዝሙር 28:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለ ፈጸሙት በደል ተገቢ ዋጋቸውን ክፈላቸው፤ በእጃቸው ስለ ፈጸሙት ክፉ ሥራ ፍረድባቸው፤ ተገቢ ቅጣታቸውንም ስጣቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንደ ሥራቸው፣ እንደ ክፉ ተግባራቸው ክፈላቸው፤ እንደ እጃቸው ሥራ ስጣቸው፤ አጸፋውን መልስላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደ ሥራቸው እንደ አካሄዳቸውም ክፋት ስጣቸው፥ እንደ እጃቸውም ሥራ ስጣቸው፥ ፍዳቸውን ወደ ራሳቸው መልስ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔር ቃል በኀይል ነው፤ የእግዚአብሔር ቃል በታላቅ ክብር ነው። |
ምንም እንኳ እኔ እግዚአብሔር መርጦ የሾመኝ ንጉሥ ብሆን ዛሬ ደካማነት ተሰምቶኛል፤ እነዚህ የጸሩያ ልጆች በእኔ ላይ እጅግ የበረቱ ዐመፀኞች ሆነውብኛል፤ እነዚህን ነፍሰ ገዳዮች እግዚአብሔር ራሱ የሚገባቸውን ቅጣት ይስጣቸው!”
የደረሰብን ችግር የክፉ ሥራችንና የበደላችን ውጤት ነው፤ ሆኖም አምላካችን የቀጣኸን ልንቀጣ ከሚገባን ያነሰ ነው፤ ከዚህም በላይ ከሞት አምልጠን በሕይወት አትርፈኸናል።
እንግዲህ የእግዚአብሔርን ቸርነትና አስፈሪነት ተመልከቱ፤ አስፈሪነቱን የሚያሳየው በወደቁት ላይ ሲሆን ቸርነቱን የሚያሳየው ግን ለእናንተ ነው፤ ይህንንም የሚያደርገው እርሱን በማመን ጸንታችሁ ብትኖሩ ነው፤ ባትጸኑ ግን እናንተም ተቈርጣችሁ ትወድቃላችሁ።
በሰጠችው መጠን ስጥዋት፤ ባደረገችውም ሥራ እጥፍ ክፈልዋት፤ እርስዋ ልዩ ልዩ መጠጦችን በቀላቀለችበት ጽዋ ውስጥ እጥፍ ኀይለኛ አድርጋችሁ ቀላቅሉባት፤