መዝሙር 27:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሐሰት ምስክሮች ዐመፅን እየተናገሩ በእኔ ላይ ስለ ተነሡ ለጠላቶቼ ፍላጎት አሳልፈህ አትስጠኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለጠላቶቼ ፍላጎት አሳልፈህ አትስጠኝ፤ የሐሰት ምስክሮች ተነሥተውብኛልና፣ ዐመፃ የሚረጩ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሐሰት ምስክሮችና ዓመፀኞች ተነሥተውብኛልና ለጠላቶቼ ፍላጎት አሳልፈህ አትስጠኝ። |
ብዙ ጊዜ በየምኲራቡ እንዲቀጡና በጌታ ላይ የስድብ ቃል እንዲናገሩ አስገድዳቸው ነበር፤ በእነርሱ ላይ በጣም ተቈጥቼም ወደ ሌሎች የውጪ አገር ከተሞች እንኳ ወጥቼ እየሄድኩ አሳድዳቸው ነበር።
ንጉሥ ሆይ! የምልህን አድምጠኝ! አንተን በእኔ ላይ ያነሣሣህ እግዚአብሔር ቢሆን ኖሮ፥ መሥዋዕት በማቅረብ ቊጣውን እንዲመልስ ማድረግ በተቻለ ነበር፤ ነገር ግን ይህን ያደረጉት ሰዎች ከሆኑ ሄደህ ባዕዳን አማልክትን አምልክ ብለው እግዚአብሔር ከሰጠኝ ርስት ድርሻ ስላባረሩኝ በእግዚአብሔር ፊት የተረገሙ ይሁኑ።