እኔ ብቸኛና ችግረኛ ስለ ሆንኩ አምላክ ሆይ! ወደ እኔ ተመለስ፤ በጎነትንም አድርግልኝ።
እኔ ብቸኛና የተጨነቅሁ እንደ መሆኔ፣ ወደ እኔ ተመለስ፤ ምሕረትም አድርግልኝ።
እኔ ብቸኛና የተጨነቅሁ ነኝና ፊትህን ወደ እኔ መልስ ማረኝም።
እኔ ድኻና ምስኪን ነኝ፤ የደረሰብኝም መከራ ልቤን አቊስሎታል።
ወደ እኔ ተመለስ፤ ለሚወዱህ ሁሉ እንደምታደርገውም ምሕረት አድርግልኝ።
ከዚህም የተነሣ መንፈሴ በውስጤ ዛለብኝ፤ ልቤም ተስፋ ቈረጠ።
በዚያን ጊዜ ኃጢአቴን ለአንተ ተናዘዝኩ፤ በደሌንም ከአንተ አልሰወርኩም፤ ኃጢአቴን ሁሉ ለአንተ ለመናዘዝ ወሰንኩ፤ አንተም ኃጢአቴን ሁሉ ይቅር አልክልኝ።
አምላክ ሆይ! እስከ አሁን ጣልከን፤ ሰባበርከን፤ እስከ አሁን ተቈጣኸን፤ አሁን መልሰን።
እግዚአብሔር ሆይ! ችግረኛና ድኻ ስለ ሆንኩ እባክህ ጸሎቴን ስማ፤ መልስም ስጠኝ።
ወደ እኔ ተመልሰህ ራራልኝ፤ ለእኔ ለአገልጋይህ ብርታትን ስጠኝ፤ እኔን የሴት አገልጋይህን ልጅ አድነኝ።
አምላክ ሆይ! ጸሎቴንና ልመናዬን ስማ፤ ስለ ስምህ ስትል ለፈረሰው ቤተ መቅደስህ ራራ።
እንደገና ትራራልናለህ፤ በደላችንን በእግርህ ሥር ጥለህ ትረግጣለህ፤ ኃጢአታችንንም ሁሉ ወደ ጥልቅ ባሕር ትጥላለህ።