መዝሙር 18:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መከራ በደረሰብኝ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራሁት፤ እንዲረዳኝም አምላኬን ለመንኩት፤ በመቅደሱ ሆኖ ድምፄን ሰማ፤ ጩኸቴንም አደመጠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በተጨነቅሁ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራሁት፤ እንዲረዳኝም ወደ አምላኬ ጮኽሁ፤ እርሱም ከመቅደሱ ድምፄን ሰማ፤ ጩኸቴም በፊቱ ከጆሮው ደረሰ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሲኦል ገመዶች ተበተቡኝ፥ የሞት ወጥመዶችም ደረሱብኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አወጣጡ ከሰማያት ዳርቻ ነው፥ መግቢያውም እስከ ዓለም ዳርቻ ነው፤ ከትኩሳቱም የሚሰወር የለም። |
ካህናቱና ሌዋውያኑም ቆመው የእግዚአብሔር በረከት በሕዝቡ ላይ እንዲወርድ ጸለዩ፤ እግዚአብሔርም በተቀደሰ መኖሪያው በሰማይ ሆኖ ጸሎታቸውን ሰማ።
ከብዙ ዓመቶች በኋላ የግብጽ ንጉሥ ሞተ፤ እስራኤላውያን ግን አሁንም በባርነት ቀንበር ሥር በመጨነቅ ርዳታ ለማግኘት በመጮኽ ላይ ነበሩ፤ ጩኸታቸውም ወደ እግዚአብሔር ደረሰ።
እንዲህም አለ፤ “አባት ሆይ፥ ሁሉ ነገር ይቻልሃል፤ ይህን የመከራ ጽዋ ከእኔ አርቅልኝ፤ ነገር ግን እንደ አንተ ፈቃድ እንጂ እንደ እኔ ፈቃድ አይሁን።”
በሰማይ ያለው የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስም ተከፈተ፤ የእርሱም የኪዳን ታቦት በቤተ መቅደሱ ውስጥ ታየ። መብረቅ፥ ድምፅ፥ ነጐድጓድ፥ የምድር መናወጥና ታላቅም በረዶ ሆነ።