La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መዝሙር 18:34 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እጆቼን ለጦርነት ያሠለጥናል፤ የነሐስን ቀስት መሳብ እንዲችሉ ክንዶቼን ያበረታል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እጆቼን ለጦርነት ያሠለጥናቸዋል፤ ክንዶቼም የናስ ቀስት መገተር ይችላሉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እግሮቼን እንደ ብሖር እግሮች የሚያበረታ በኮረብቶችም የሚያቆመኝ እግዚአብሔር ነው።

Ver Capítulo



መዝሙር 18:34
8 Referencias Cruzadas  

አምላኬ ሆይ! የማዳን ጋሻህ ሰጠኸኝ፤ የአንተ ኀይልም ያጸናኛል።


መጠጊያዬ እግዚአብሔር ይመስገን! ለሰልፍ ያሠለጥነኛል፤ ለጦርነትም ያዘጋጀኛል።


እርሱ በመላው ዓለም የሚካሄደውን ጦርነት ሁሉ ያቆማል፤ ቀስትንና ጦርን ይሰብራል፤ ጋሻንም በእሳት ያቃጥላል።


በዳኝነት ለሚያገለግሉት የፍትሕ ጥበብ ይሰጣቸዋል፤ የከተማይቱን የቅጽር በሮች ከጠላት ለሚከላከሉትም ኀይልን ይሰጣቸዋል።


ሕዝቦች በሥልጣኑ ሥር እንዲገዙ ለማድረግ፥ ነገሥታትን ከሥልጣን እንዲያወርድ፥ የከተሞችን ቅጽር በሮች ይከፍትለት ዘንድ ቀኝ እጁን ለያዘውና ቀብቶ ላነገሠው ንጉሥ ቂሮስን እግዚአብሔር እንዲህ ይለዋል፦


“ዔላምን ይህን ያኽል ኀያል እንድትሆን ያደረጋችኹትን የዔላምን የጦር ኀይል እሰብራለሁ።


በዚያን ጊዜ በኢይዝራኤል ሸለቆ የእስራኤልን ጦር እደመስሳለሁ፤ ስለዚህ የልጅህን ስም ‘ኢይዝራኤል’ ብለህ ጥራው።”


ጌታ እግዚአብሔር ብርታቴ ነው፤ እግሮቼንም እንደ ዋልያ እግሮች ያጠነክርልኛል፤ በተራሮችም ላይ እንድራመድ ያደርገኛል።