መዝሙር 149:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር በሕዝቡ ደስ ይለዋል፤ ድል በማቀዳጀት ትሑታንን ያከብራቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር በሕዝቡ ደስ ይለዋልና፤ የዋሃንንም በማዳኑ ውበት ያጐናጽፋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ በሕዝቡ ተደስቶአልና፥ የዋሃንንም በማዳኑ ያስጌጣቸዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር በሕዝቡ ደስ ብሎታልና፥ የዋሃንንም በማዳኑ ከፍ ከፍ ያደርጋልና። |
ድል ማድረጌ የሚያስደስታቸው ሁሉ ደስ ይበላቸው፤ “እግዚአብሔር ታላቅ ነው! ለአገልጋዩ ሁኔታዎች ሁሉ ሲሳኩለት እግዚአብሔር ደስ ይለዋል!” ይበሉ።
እኔ በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፤ ሁለንተናዬም በአምላኬ ሐሴትን ያደርጋል፤ የአበባ አክሊል በራሱ ላይ እንደሚያደርግ ሙሽራ፥ በጌጣጌጥም እንዳሸበረቀች ሙሽሪት አድርጎ፥ የመዳንን ልብስ አልብሶኛል፤ የጽድቅንም መጐናጸፊያ ደርቦልኛል።
እግዚአብሔር አምላክሽ ከአንቺ ጋር ነው፤ በኀይሉም ድልን ያጐናጽፍሻል፤ እግዚአብሔር በአንቺ ደስ ይለዋል፤ በፍቅሩም ያድስሻል፤ ሕዝቦች በበዓል ቀን በመዝሙር እንደሚያደርጉት፥ እርሱ በአንቺ ይደሰታል።”
ነገር ግን ውበታችሁ በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ በከበረና በማይጠፋው ጌጥ በገርነትና በጭምትነት መንፈስ ያጌጠው፥ በልብ ተሰውሮ የሚገኘው፥ ውስጣዊ ሰውነት ይሁን።
እንዲሁም እናንተ ጐልማሶች! ለሽማግሌዎች ታዘዙ፤ ሁላችሁም ትሕትናን እንደ ልብስ ለብሳችሁ አንዱ ሌላውን ያገልግል፤ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል ለትሑቶች ግን ጸጋን ይሰጣል” ተብሎ ተጽፎአልና።
እኔም “ጌታ ሆይ፥ አንተ ታውቃለህ” አልኩት። እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “እነዚህ ታላቁን መከራ አልፈው የመጡ ናቸው፤ ልብሳቸውንም በበጉ ደም አጥበው ነጭ አድርገውታል፤