መዝሙር 148:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አራዊትና ለማዳ እንስሶች፥ በምድር የምትሳቡና በክንፍ የምትበርሩ ፍጥረቶች ሁሉ እግዚአብሔርን አመስግኑት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዱር አራዊትና የቤት እንስሳት ሁሉ፣ በምድር የሚሳቡ ፍጥረታትና የሚበርሩ ወፎችም፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አራዊትና እንስሳት ሁሉ፥ የሚሳቡና የሚበርሩ ወፎችም፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አራዊትም፥ እንስሳትም ሁሉ፥ ተንቀሳቃሾችም፥ የሚበርሩ ወፎችም፤ |
ለተመረጡት ሕዝቤ ውሃን ለመስጠት ወንዞች በበረሓ ጅረቶች በምድረ በዳ እንዲፈስሱ ባደረግሁ ጊዜ የምድር አራዊት እንኳ ሳይቀሩ ያከብሩኛል፤ ቀበሮዎችና ሰጎኖችም ያመሰግኑኛል።
የምተክለው በእስራኤል በሚገኝ በከፍተኛ ተራራ ላይ ነው፤ ይህንንም የማደርገው ቅርንጫፎችን አስገኝቶ ፍሬ በማፍራት የተዋበ የሊባኖስ ዛፍ እንዲሆን ነው። በሥሩም የተለያዩ ወፎች ይኖሩበታል፤ በቅርንጫፎቹም ጥላ ሥር ክንፍ ያላቸው ፍጥረቶች ሁሉ ጎጆዎቻቸውን ይሠሩበታል።