መዝሙር 147:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን ያድሳል፤ ከእስራኤል የተሰደዱትንም ይመልሳል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን መልሶ ይሠራታል፤ ከእስራኤል የተበተኑትን ይሰበስባል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ኢየሩሳሌምን ይሠራል፥ ከእስራኤልም የተበተኑትን ይሰበስባል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጽዮንም ሆይ፥ አምላክሽን አመስግኚ፤ የደጆችሽን መወርወሪያ አጽንቶአልና፥ ልጆችሽንም በውስጥሽ ባርኮአልና። |
በዙሪያችን የሚኖሩ አሕዛብ ጠላቶቻችን ይህን በሰሙ ጊዜ ሥራው አስደናቂ ሥራ መሆኑን ስለ ተገነዘቡና፤ ሥራውም በእግዚአብሔር ርዳታ የተከናወነ መሆኑን ስለ ተረዱ እጅግ ፈርተው ተደናገጡ።
ከፍልስጥኤም ለሚመጡ መልእክተኞች የምንሰጠው መልስ ምንድን ነው? እግዚአብሔር ጽዮንን እንደገና መመሥረቱንና በሥቃይ ይኖሩ የነበሩ ሕዝቡ መጠጊያ አግኝተው በሰላም እንዲኖሩ ማድረጉን እንነግራቸዋለን።
በዚያም ዘመን ትልቅ መለከት ይነፋል፤ በአሦር ምድር ጠፍተው የነበሩትና ወደ ግብጽ ተሰደው የነበሩት እስራኤላውያንም ተመልሰው በኢየሩሳሌም በሚገኘው በተቀደሰው ተራራ ላይ ይሰግዳሉ።
የተበተኑትን እስራኤላውያንን የሚሰበስበው ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ከተሰበሰቡት ሌላ ሌሎችንም ወገኖች ወደ እነርሱ ሰብስቤ አመጣቸዋለሁ።”
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሕዝቦች ሆይ! አድምጡኝ፤ በሩቅ ጠረፎችም ቃሌን ዐውጁ፤ እኔ ሕዝቤን በትኜ ነበር፤ አሁን ግን እሰበስባቸዋለሁ፤ እረኛ መንጋውን እንደሚጠብቅም እጠብቃቸዋለሁ።
እንደ እሳት በሚነደው ታላቅ ቊጣዬ የበተንኳቸውን ሕዝብ ከተበተኑባቸው አገሮች ሁሉ እንደገና ወደዚህ ቦታ እሰበስባቸዋለሁ፤ በሰላም እንዲኖሩም አደርጋለሁ።
መዘጋጀትም ያለበት ከብዙ ጊዜ በኋላ በጦርነት ወድማ የነበረችውን የእስራኤልን ምድር እንዲወር ስለማዘው ነው፤ ለብዙ ጊዜ ባድማ ሆና ነበር፤ ሕዝብዋ ይኖሩባቸው ከነበሩት አገሮች ተመልሰዋል፤ አሁን እስራኤላውያን በሀገራቸው ውስጥ በሚገኙ ተራራዎች ላይ በሰላም ይኖራሉ።
ይህን ልብ ብለህ አስተውል፤ ኢየሩሳሌም እንድትታደስ ትእዛዝ ከወጣበት ጊዜ አንሥቶ መሲሕ እስከሚመጣበት ጊዜ ድረስ ሰባት ሳምንቶች ያልፋሉ፤ እንዲሁም ለሥልሳ ሁለት ሳምንት በችግር ጊዜ ኢየሩሳሌም፥ መንገዶችዋና የመከላከያ ጒድጓድዋ ይገነባሉ። ይሁን እንጂ ይህ ሁሉ የመከራ ዘመን ይሆናል።
እኔም እንዲህ እልሃለሁ፤ አንተ (ጴጥሮስ)፥ አለት ነህ፤ በዚህችም የመሠረት ድንጋይ ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፤ ይህችንም ቤተ ክርስቲያን የሞት ኀይል እንኳ አያሸንፋትም።