እግዚአብሔር ሆይ! ሰማይን ሰንጥቀህ ውረድ፤ ተራራዎችን ዳስስ፤ እነርሱም ይጢሱ።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ሰማያትህን ሰንጥቀህ ውረድ፤ ይጤሱም ዘንድ ተራሮችን ዳስስ።
አቤቱ፥ ሰማዮችህን ዝቅ ዝቅ አድርጋቸው ውረድም፥ ተራሮችን ዳስሳቸው ይጢሱም።
የቅድስናህንም ክብር ታላቅነት ይናገራሉ፥ ተአምራትህንም ያስረዳሉ።
ምድርን ሲመለከት ትንቀጠቀጣለች፤ ተራራዎችን ሲነካ እነርሱም ይጤሳሉ።
በኪሩቤል ላይ ሆኖ በረረ፤ በነፋስ ክንፎች ላይ ሆኖ ወደ ላይ መጠቀ።
ሰማይን ሰንጥቆ ወደ ታች ወረደ፤ ከእግሩም በታች ጥቅጥቅ ያለ ደመና ነበረ።
እግዚአብሔር በእሳት ስለ ወረደበት መላው የሲና ተራራ በጢስ ተሞላ። ጢሱም ከእሳት ምድጃ እንደሚወጣ ዐይነት ሆኖ ወደ አየር ተትጐለጐለ፤ ሰዎቹም እጅግ ፈርተው ተንቀጠቀጡ።
እናንተ በእጅ ወደሚዳሰሰው ወይም ወደሚቃጠለው ወደ ሲና ተራራ አልደረሳችሁም፤ ወደ ጭጋጉ፥ ወደ ጨለማውም፥ ወደ ዐውሎ ነፋሱም፥