ከብዙ ጊዜ በፊት የነበረውን አስታውሳለሁ፤ ሥራዎችህንም ሁሉ አሰላስላለሁ፤ የእጅህን ሥራዎች ሁሉ አስተውላለሁ።
የቀድሞውን ዘመን አስታወስሁ፤ ሥራህንም ሁሉ አሰላሰልሁ፤ የእጅህንም ሥራ አውጠነጠንሁ።
የቀድሞውን ዘመን አሰብሁ፥ ሥራህንም ሁሉ አሰላሰልሁ፥ የእጅህንም ሥራ አስተዋልሁ።
አቤቱ፥ ሰማዮችህን ዝቅ ዝቅ አድርጋቸው፥ ውረድም፤ ተራሮችን ዳስሳቸው፥ ይጢሱም።
ከዕለታት አንድ ቀን ወደ ማታ ጊዜ እያሰላሰለ በመስክ ውስጥ ሲዘዋወር ሳለ ግመሎች ሲመጡ በሩቅ አየ።
እግዚአብሔር ቸርና መሐሪ ነው፤ በአስደናቂ ሥራውም የገነነ ነው።
አምላኬ ሆይ! ተስፋ ቈርጬአለሁ ስለዚህም ከዮርዳኖስና ከሔርሞን ምድር ከሚዛር ተራራ አስብሃለሁ።
ሕዝቤ ሆይ! የሞአብ ንጉሥ ባላቅ ምን እንደ ዐቀደብህና የቢዖር ልጅ በለዓም ምን እንደ መለሰለት አስታውስ፤ ከሺጢም ተነሥተህ ወደ ጌልጌላ በምትሄድበት ጊዜ በመንገድ ላይ የሆነውን ሁሉ አስታውስ፤ ይህን ሁሉ ብታስታውስ አንተን ለማዳን ያደረግኹትን ሁሉ ታውቃለህ።”