መዝሙር 140:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእሳት ፍም በላያቸው ይውደቅ፤ ወደ ጒድጓድም ይጣሉ፤ ከዚያም ከቶ አይውጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእሳት ፍም በላያቸው ይውረድ፤ ዳግመኛም እንዳይነሡ ወደ እሳት ይጣሉ፤ ማጥ ወዳለበት ጕድጓድ ይውደቁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሚከብቡኝ ራሳቸውን አነሡ፥ የከንፈራቸው ክፋት ይክደናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ ብቻዬን እስካልፍ ድረስ ኃጥኣን በወጥመዳቸው ይውደቁ። |
አምላክ ሆይ! አንተ ግን ክፉዎችን ወደ ጥልቅ ጒድጓድ ትጥላቸዋለህ፤ እነዚያ ነፍሰ ገዳዮችና ከዳተኞች ግማሽ ዕድሜአቸውን እንኳ አይኖሩም፤ እኔ ግን በአንተ እተማመናለሁ።
ነገር ግን ፈሪዎች፥ እምነተ ቢሶች፥ ርኩሶች፥ ነፍሰ ገዳዮች፥ አመንዝሮች፥ አስማተኞች፥ ጣዖት አምላኪዎች፥ ውሸታሞች ሁሉ ዕጣ ክፍላቸው በዲን በሚቃጠለው በእሳት ባሕር ውስጥ ይሆናል፤ ይህም ሁለተኛው ሞት ነው።”