መዝሙር 14:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እግዚአብሔር ክፉ አድራጊዎች ከቶ አያስተውሉምን? ሰዎች እንጀራን እንደሚበሉ ክፉ አድራጊዎች ሕዝቤን ይበዘብዛሉ፤ እነርሱም ወደ እኔ ወደ እግዚአብሔር አይጸልዩም።” ይላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕዝቤን እንደ እንጀራ የሚበሉት፣ እግዚአብሔርንም የማይጠሩት፣ እነዚህ ክፉ አድራጊዎች ምንም አያውቁምን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክፉ አድራጊዎች አያስተውሉምን? እንጀራን እንደሚበሉ ሕዝቤን የሚያኝኩ፥ ጌታን አይጠሩምን፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኀጢአተኛ በፊቱ የተናቀ፥ እግዚአብሔርንም የሚፈሩትን የሚያከብር፥ ለባልንጀራው ምሎ የማይከዳ። |
የዛፍ ቅርንጫፎች በሚደርቁበትም ጊዜ ይሰባበራሉ፤ ሴቶችም ለእሳት ማገዶ ይለቅሙአቸዋል፤ ሕዝቡ ማስተዋል ስለ ጐደለው ፈጣሪ አምላኩ አይራራለትም፤ ምንም ምሕረት አያደርግለትም።
አስደናቂ ተአምርን አከታትዬ በማምጣት ይህ ሕዝብ እንዲገረም አደርገዋለሁ፤ የጥበበኞች ጥበብ ትሰወራለች፤ የአስተዋዮችም ማስተዋል ትረሳለች።”
“ከየሀገሩ ከስደት ተርፋችሁ የተመለሳችሁ፥ ተሰብስባችሁ በአንድነት ቅረቡ! የእንጨት ጣዖቶችን ይዘው የሚዘዋወሩና ማዳን ወደማይችል ጣዖት የሚጸልዩ ዕውቀት የሌላቸው ናቸው።
እኛ ሁላችን በኃጢአት ረክሰናል፤ ጽድቃችንም እንደ አደፍ ጨርቅ ሆኖአል፤ ከኃጢአታችን ብዛት የተነሣ ደርቀው በነፋስ እንደሚረግፉ ቅጠሎች ሆነናል።
በኃጢአታችን ምክንያት ፊትህን ስላዞርክብንና ለበደላችንም ተገዢዎች እንድንሆን ስለ ተውከን ስምህን የሚጠራና አንተን ለማግኘት የሚጥር ማንም የለም።
ቊጣህን አንተን በማያውቁና ስምህን በማይጠሩ ሕዝቦች ላይ አፍስሰው፤ እነርሱ ሕዝብህን ፈጅተዋል፤ ሁላችንንም ፈጽመው በመደምሰስ፥ አገራችንን አውድመዋል።
“ሁሉም በቊጣ እንደ ምድጃ ግለው ገዢዎቻቸውን ፈጁ፤ ንጉሦቻቸውንም በየተራ አጠፉ፤ ይህም ሁሉ ሲሆን ከእነርሱ አንድ እንኳ የእኔን ርዳታ የጠየቀ የለም።”