መዝሙር 135:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በግብጽ አገር የሰዎችንና የእንስሶችን የበኲር ልጆችን የገደለ እርሱ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በኵር ሆኖ በግብጽ የተወለደውን፣ ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ ቀሠፈ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የግብጽን በኩር ልጆች ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ መታ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለፀሐይ ቀንን ያስገዛው፤ ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፤ |
“በዚያችም ሌሊት እኔ በግብጽ ምድር ሁሉ እየተላለፍኩ እያንዳንዱን የሰውም ሆነ የእንስሳ ዘር የሆነውን የበኲር ልጅ ሁሉ እገድላለሁ፤ የግብጽንም አማልክት ሁሉ እቀጣለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።
የግብጽ ንጉሥ ልቡን አደንድኖ እልኸኛ በመሆን አለቃችሁም ባለ ጊዜ እግዚአብሔር በግብጽ ምድር የሰውንም ሆነ የእንስሶችን በኲር ሁሉ ገደለ፤ በኲር ሆኖ የተወለደውን ወንድ እንስሳ መሥዋዕት አድርጌ የማቀርበው በዚህ ምክንያት ነው፤ በኲር ሆነው የተወለዱትን ወንዶች ልጆቻችንን ግን እንዋጃቸዋለን።
ቀጥሎም ‘ባሪያ አድርጎ በሚገዛው ሕዝብ ላይ እፈርድበታለሁ፤ ከዚያም በኋላ ነጻ ወጥተው በዚህ ስፍራ ያመልኩኛል’ ብሎ እግዚአብሔር ተናግሮአል።