መዝሙር 133:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሔርሞን ተራራ ወደ ጽዮን ኰረብቶች እንደሚንጠባጠብ ጤዛ ነው፤ እግዚአብሔር ዘለዓለማዊ የሆነውን ሕይወትና በረከት የሚሰጠው በዚያ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም በጽዮን ተራራ ላይ እንደሚወርድ፣ እንደ አርሞንዔም ጠል ነው፤ በዚያ እግዚአብሔር በረከቱን፣ ሕይወትንም እስከ ዘላለም አዝዟልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጽዮን ተራሮች እንደሚወርድ እንደ አርሞንዔም ጠል ነው፥ በዚያ ጌታ በረከቱን ሕይወትንም እስከ ዘለዓለም አዝዞአልና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰማይንና ምድርን የሠራ እግዚአብሔር ከጽዮን ይባርክህ። |
ከሞት የተረፉትም የእስራኤል ሕዝብ በብዙ ሕዝቦች መካከል እግዚአብሔር እንደሚልከው ጠልና በሣር እንደሚወርድ ካፊያ ይሆናሉ፤ ተማምነው የሚጠባበቁት ሰውን ሳይሆን እግዚአብሔርን ብቻ ይሆናል።
እኔ ከምሰጠው ውሃ የሚጠጣ ለዘለዓለም ከቶ አይጠማም፤ እኔ የምሰጠው ውሃ፥ ለሚጠጣው ሰው ለዘለዓለም ሕይወት የሚፈልቅ የውሃ ምንጭ ይሆናል።”
“እውነት፥ እውነት እላችኋለሁ፤ ቃሌን የሚሰማና በላከኝም የሚያምን የዘለዓለም ሕይወት አለው፤ እርሱ ከሞት ወደ ሕይወት የተሻገረ ስለ ሆነ አይፈረድበትም።
ይህም የሆነው በሞት ምክንያት ኃጢአት እንደ ነገሠ ሁሉ እንዲሁም በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ዘለዓለማዊ ሕይወት እንዲገኝ የእግዚአብሔር ጸጋ ጽድቅን በመስጠት ይነግሣል።
ከኃጢአት የሚገኘው ዋጋ ሞት ነው፤ ከእግዚአብሔር የሚሰጠው ስጦታ ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት የሚገኘው የዘለዓለም ሕይወት ነው።
ይህም ምድር ከዓሮዔር ከተማ በመነሣት በአርኖን ወንዝ ጫፍ አልፎ በሰሜን በኩል እስከ ሢርዮን ተራራ የሚደርስ ነው፤ ይህም የሢርዮን ተራራ ተብሎ የሚጠራው የሔርሞን ተራራ ነው።