መዝሙር 129:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በቤት ጣራ ላይ እንደሚበቅልና ከማደጉ በፊት እንደሚደርቅ ሣር ይሁን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ገና ከመብቀሉ እንደሚደርቅ፣ በጣራ ላይ እንደ በቀለ ሣር ይሁኑ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሰገነት ላይ እንደ በቀለ ሣር፥ ሳይነቀል እንደሚደርቅ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከማለዳው ሰዓት ጀምሮ እስከ ሌሊት ነፍሴ በእግዚአብሔር ታመነች። ከማለዳ ጀምሮ እስራኤል በእግዚአብሔር ታመነ። |
የእነዚያ አገር ነዋሪዎች ኀይላቸው ተዳክሞ፥ ተስፋ በመቊረጥ እንዳያፍሩ ተደርገው በምሥራቅ ነፋስ እንደ ተመቱ፥ የመስክ አትክልቶች፥ እንደ ቀጨጩ አረንጓዴ ቡቃያዎች፥ በጣራ ላይ እንደ በቀለ ሣር ናቸው።
የሕዝቦቻቸው ኀይል ተዳክሞአል፤ እነርሱም ተስፋ ቈርጠው ዐፍረዋል፤ እንደ ሜዳ አበባ፥ እንደ ለጋ ሣር፥ በጣራ ላይ እንደሚበቅልና ፈጥኖ እንደሚጠወልግ ጓሳ ናቸው።