እግዚአብሔር ሆይ! ትእዛዞችህን ለሚፈጽሙ ደጋግ ሰዎች ቸርነት አድርግላቸው።
እግዚአብሔር ሆይ፤ መልካም ለሆኑ፣ ልባቸውም ለቀና መልካም አድርግ።
አቤቱ፥ ለመልካሞች፥ ልባቸውም ለቀና መልካምን አድርግ።
አቤቱ፥ በአዜብ እንዳሉ ፈሳሾች ምርኮአችንን መልስ።
አንተ ቸር ስለ ሆንክ ቸር የሆነውን ታደርጋለህ፤ ሕጎችህን አስተምረኝ።
ኀፍረት እንዳይደርስብኝ ሕግህን በትክክል እንድፈጽም እርዳኝ።
እግዚአብሔር ኃጢአቱን የማይቈጥርበት ከሽንገላም የራቀ ሰው የተባረከ ነው።
ለሚያውቁህ ዘለዓለማዊ ፍቅርህ አይቋረጥባቸው፤ አዳኝነትህም ለልበ ቅኖች ይቀጥል።
አምላክ ሆይ! ጽዮንን ለመርዳት፥ የኢየሩሳሌምን ቅጥሮች ለመገንባት እባክህ ፈቃድህ ይሁን።
ልባቸው ቅን የሆኑትን የሚያድን፥ ልዑል እግዚአብሔር፥ እርሱ ጋሻዬ ነው።
ልባቸው ንጹሕ ለሆነ እስራኤላውያን እግዚአብሔር ቸር ነው።
ጌታችንና አምላካችን ሆይ! አንተ እንደ ፀሐይና እንደ ጋሻ ነህ፤ በቸርነትና በክብር ትጠብቀናለህ፤ ደግ ለሚሠሩ ሰዎች ማናቸውንም መልካም ነገር አትከለክላቸውም።
የሠራዊት አምላክ ሆይ! በአንተ የሚታመኑ እንዴት የተባረኩ ናቸው!
ፍትሕ እንደገና የዳኝነት መሠረት ትሆናለች፤ ልበ ቅኖችም ሁሉ ይደግፉአታል።
እግዚአብሔር በተስፋ ለሚጠባበቁትና እርሱን ለሚፈልጉ መልካም ነው።
ናትናኤል ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ ኢየሱስ “እነሆ! ተንኰል የሌለበት እውነተኛ የእስራኤል ሰው!” ሲል ስለ እርሱ ተናገረ።
እግዚአብሔር ቅን ፈራጅ ነው፤ ስለዚህ ሥራችሁንና በፊትም ሆነ አሁን ቅዱሳንን በመርዳት ስለ ስሙ ያሳያችሁትን ፍቅር አይረሳም።
እነርሱ ሐሰት ተናግረው አያውቁም፤ ነቀፋም የሌለባቸው ናቸው።