ኢየሩሳሌም ሆይ! በበሮችሽ ገብተን በውስጥ ቆመናል።
ኢየሩሳሌም ሆይ፤ እግሮቻችን ከደጅሽ ውስጥ ቆመዋል።
ኢየሩሳሌም ሆይ፥ እግሮቻችን በአደባባይሽ ቆሙ።
እነሆ፥ የባሪያዎች ዐይኖች ወደ ጌቶቻቸው እጅ እንደ ሆኑ፥ የባሪያዪቱም ዐይን ወደ እመቤቷ እጅ እንደ ሆነ፥ እንዲሁም ይቅር እስከሚለን ድረስ ዐይኖቻችን ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ናቸው።
አሁን ግን ስሜ እንዲጠራበት ኢየሩሳሌምን፥ ሕዝቤን እንድትመራም አንተን ዳዊትን መርጬአለሁ።’ ”
እያመሰገናችሁ በመቅደሱ በሮች ግቡ፤ ምስጋናም በመስጠት ወደ አደባባዩ ሂዱ፤ አመስግኑት፤ ስሙንም አወድሱ።
በመጓዝ ላይ ሳሉ ብዙ ብርታትን ያገኛሉ፤ የአማልክትንም አምላክ በጽዮን ያዩታል።
ለእኔ ከጭቃ የተሠራ መሠዊያ አብጁልኝ፤ በእርሱም ላይ ከበጎቻችሁ፥ ከፍየሎቻችሁና ከከብቶቻችሁ መርጣችሁ የሚቃጠልና የአንድነት መሥዋዕት አድርጋችሁ ሠዉበት፤ ስሜ እንዲታሰብበት በወሰንኩት ስፍራ ሁሉ ወደ እናንተ መጥቼ እባርካችኋለሁ፤