ወደ ውስጥ ገብቼ እግዚአብሔርን እንዳመሰግን የቤተ መቅደስን በሮች ከፈቱልኝ።
የጽድቅን ደጆች ክፈቱልኝ፤ በዚያ ገብቼ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ።
የጽድቅን ደጆች ክፈቱልኝ፥ ወደ እነርሱ ገብቼ ጌታን አመሰግናለሁ።
እኔ በምድር ስደተኛ ነኝ፤ ትእዛዛትህን ከእኔ አትሰውር።
እያመሰገናችሁ በመቅደሱ በሮች ግቡ፤ ምስጋናም በመስጠት ወደ አደባባዩ ሂዱ፤ አመስግኑት፤ ስሙንም አወድሱ።
በተቀደሰ መኖሪያው ያለ አምላክ አባት ለሌላቸው ልጆች አባት ነው፤ ባሎቻቸው ለሞቱባቸውም ሴቶች ጠባቂ ነው።
ወደ ፊቱ ቀርበን እናመስግነው፤ በዝማሬም ለእርሱ እልል እንበል!
እምነቱን የጠበቀ እውነተኛ ሕዝብ እንዲገባ የከተማይቱን በሮች ክፈቱ፤
እግዚአብሔር ያድነኛል፤ ስለዚህ እኛ በሕይወት ዘመናችን ሁሉ አውታር ባለው የሙዚቃ መሣሪያ የምሥጋና መዝሙር በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንዘምራለን።
ንጉሥ ሕዝቅያስም “ድኜ ወደ ቤተ መቅደስ ለመሄድ እንደምችል የማውቀው በምን ምልክት ነው?” ሲል ኢሳይያስን ጠየቀ።
ከሕይወት ዛፍ ፍሬ ለመብላትና በደጃፎችዋም ወደ ከተማይቱ ለመግባት መብት እንዲኖራቸው ልብሳቸውን ያጠቡ የተባረኩ ናቸው።