ብዙ ሕዝቦች ከበውኝ ነበር፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ኀይል ደመሰስኳቸው።
ሕዝቦች ሁሉ ከበቡኝ፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ስም አስወግዳቸዋለሁ።
አሕዛብ ሁሉ ከበቡኝ፥ በጌታ ስም አጠፋኋቸው፥
በፍጹም ልቤ ፈለግሁህ፥ ከትእዛዝህ አታርቀኝ።
ጠላቶቼ ከፊቴ ወደ ኋላ እንዲሸሹ አደረግህ የሚጠሉኝንም ሁሉ አጠፋቸዋለሁ።
የሚረዳቸውን በመፈለግ ይጮኻሉ፤ ነገር ግን ማንም አያድናቸውም፤ እግዚአብሔርንም ይጠሩታል፤ እርሱ ግን አይመልስላቸውም።
እነርሱ ቀኑን ሙሉ እንደ ጐርፍ ከበቡኝ፤ ፈጽመውም አሰጠሙኝ።
የቅርብ ወዳጆቼንና ጓደኞቼን ከእኔ አርቀህ ጨለማ ብቻ ከእኔ ጋር እንዲቀር አደረግህ።
በዚያን ቀን ኢየሩሳሌምን ለአሕዛብ ሁሉ እንደ ከባድ ድንጋይ አደርጋታለሁ፤ እርስዋን ለማንሣት የሚሞክር ሁሉ ራሱን ይጐዳል፤ የዓለም ሕዝቦች ሁሉ እርስዋን ለማጥቃት ተባብረው ይመጣሉ፤
እነዚህም ሁሉ ነገሥታት ኀይላቸውን አስተባብረው እስራኤላውያንን ለመውጋት በሜሮም ምንጭ አጠገብ ሰፈሩ።