La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መዝሙር 116:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እርሱን በምጠራው ጊዜ ሁሉ ስለሚሰማኝ፥ በዘመኔ ሁሉ ወደ እርሱ እጮኻለሁ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ጆሮውን ወደ እኔ አዘንብሏልና፣ በሕይወት ዘመኔ ሁሉ ወደ እርሱ እጣራለሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጆሮውን ወደ እኔ አዘንብሏልና በዘመኔ ሁሉ እጠራዋለሁ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ምሕ​ረቱ በእኛ ላይ ጸን​ታ​ለ​ችና፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እው​ነት ለዘ​ለ​ዓ​ለም ትኖ​ራ​ለች። ሃሌ ሉያ።

Ver Capítulo



መዝሙር 116:2
13 Referencias Cruzadas  

ሁሉን በሚችል አምላክ ይደሰታሉን? በየጊዜውስ የእግዚአብሔርን ስም ይጠራሉን?


የልመናዬን ድምፅ ስለ ሰማኝ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን።


ጌታ ሆይ! አድምጠኝ፤ ፈጥነህም በመምጣት አድነኝ፤ መጠጊያ አለትና ጠንካራ ምሽግ ሆነህ አድነኝ።


አንተ መጠጊያ ምሽጌ ነህ፤ ስለ ስምህ ስትል ምራኝ፤ የምሄድበትንም መንገድ አሳየኝ።


እንዲረዳኝ በትዕግሥት ጌታን ተጠባበቅሁት። ወደ እኔም መለስ ብሎ ጸሎቴን ሰማ።


አዳኜ እግዚአብሔር አምላክ ሆይ! ትረዳኝ ዘንድ በቀን ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ ሌሊቱንም በአንተ ፊት አለቅሳለሁ።


ጥልቅ ወደ ሆነው ወደ ባሕር መሠረት ጣልከኝ፤ በዙሪያዬም ውሃ ከበበኝ፤ ማዕበልህና ሞገድህ በላዬ ላይ አለፉ።


ከዚህ በኋላ፥ ኢየሱስ ሳይታክቱ ዘወትር መጸለይ እንደሚገባቸው ለማስተማር ይህን ምሳሌ ነገራቸው፤


ስለዚህ ስለ ሁሉም ነገር በጸሎት፥ በልመናና በምስጋና ለእግዚአብሔር አቅርቡ እንጂ ስለምንም ነገር አትጨነቁ።


እግዚአብሔርን ተግታችሁ በማመስገን ባለማቋረጥ ጸልዩ፤