ሕዝቅያስ ግን ልቡ በትዕቢት ተሞልቶ ስለ ነበር፥ እግዚአብሔር ስላደረገለት ቸርነት ሁሉ ተገቢ ምስጋና አላቀረበም፤ ከዚህም የተነሣ በእርሱ፥ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ሕዝብ ብርቱ ሥቃይ ደረሰባቸው።
መዝሙር 116:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስላደረገልኝ መልካም ነገር ሁሉ ለእግዚአብሔር ምን ውለታ ልመልስ እችላለሁ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለ ዋለልኝ ውለታ ሁሉ፣ ለእግዚአብሔር ምን ልክፈለው? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስላደረገልኝ መልካም ነገር ሁሉ ለጌታ ምንን እመልሳለሁ? |
ሕዝቅያስ ግን ልቡ በትዕቢት ተሞልቶ ስለ ነበር፥ እግዚአብሔር ስላደረገለት ቸርነት ሁሉ ተገቢ ምስጋና አላቀረበም፤ ከዚህም የተነሣ በእርሱ፥ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ሕዝብ ብርቱ ሥቃይ ደረሰባቸው።
ለኀያሉ አምላክ ለእግዚአብሔር ለመስገድ በምመጣበት ጊዜ ምን ይዤ ልቅረብ? ለእርሱ የሚቃጠል መሥዋዕት ይሆኑ ዘንድ የአንድ ዓመት ጥጆችን ይዤ ልምጣን?
እንግዲህ ወንድሞቼ ሆይ! እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ፥ ሕያውና የተቀደሰ መሥዋዕት አድርጋችሁ ሁለንተናችሁን እንድታቀርቡ በመሐሪው በእግዚአብሔር ስም እለምናችኋለሁ፤ ይህም ማቅረብ የሚገባችሁ ቅንነት ያለው እውነተኛ የእግዚአብሔር አገልግሎት ነው።