መዝሙር 109:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለወዳጅነቴ የመለሱልኝ አጸፋ ክስ ነው፤ እኔ ግን እጸልይላቸዋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስወድዳቸው ይወነጅሉኛል፤ እኔ ግን እጸልያለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በፍቅሬ ፋንታ ከሰሱኝ፥ እኔ ግን እጸልያለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት አንተ ለዘለዓለም ካህን ነህ ብሎ፥ እግዚአብሔር ማለ አይጸጸትምም። |
ስለዚህ ሐኑን የዳዊትን መልእክተኞች ይዞ ጢማቸውን ላጨ፤ ኀፍረተ ሥጋቸው እስኪታይ ድረስ ከወገባቸው በታች ያለውን ልብስ ቈረጠና ወደ አገራቸው ሰደዳቸው፤
ዳንኤል ዐዋጁ ተፈርሞበት እንደ ጸና ቢያውቅም እንኳ ወደሚኖርበት ሰገነት ወጣ፤ የሚኖርበትም ሰገነት በኢየሩሳሌም ትይዩ የተከፈቱ መስኮቶች ነበሩት፤ ከዚህ በፊት ያደርገው እንደ ነበረም በጒልበቱ በመንበርከክ አምላኩን እያመሰገነ በቀን ሦስት ጊዜ ይጸልይ ነበር።
ከዚህ በኋላ ኢየሱስ፦ “አባት ሆይ! የሚያደርጉትን ስለማያውቁ ይቅር በላቸው!” አለ። ወታደሮቹም ዕጣ ተጣጥለው የኢየሱስን ልብስ ተከፋፈሉ።
ስለ እናንተ እንኳን ገንዘቤን ራሴንም አሳልፌ ብሰጥ እጅግ በጣም ደስ ይለኛል፤ ታዲያ፥ እኔ ይህን ያኽል አብዝቼ ስወዳችሁ እናንተ የምትወዱኝ እንዲህ በጥቂቱ ነውን?